በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያየ ጊዜ ውርስ የተደረጉ ተሽከርካሪ እና led ceiling cristal chandeliner light በግልፅ እንዲሁም ጫማ ፣ አልባሳት ፣ TV 65 inch ፣ ፕሎፕ ጠጠር እና የወጥ ቤት እቃ በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
Kombolcha Customs Branch (የኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2018 ዓ.ም
በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያየ ጊዜ ውርስ የተደረጉ ተሽከርካሪ እና led ceiling cristal chandeliner light በግልፅ እንዲሁም ጫማ ፣ አልባሳት ፣ TV 65 inch ፣ ፕሎፕ ጠጠር እና የወጥ ቤት እቃ በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተጫራቾች መመሪያ የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን መስፈርቶቹ፡-
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የፀና የንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር መ/ቤት የሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል ሲሆን፤ ተሽከርካሪ መጫረት ለምትፈልጉ ንግድ ፈቃድ የማይጠይቅ በመሆኑ ማንኛውም እድሜው ከ-18-አመት በላይ የሆነ የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ግለሰብ መጫረት ይችላል።
- የዚህ አንቀፅ ተራ ቁጥር (1) ድንጋጌ ቢኖርም ግምታዊ ዋጋው ከብር 500 ሺህ በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት (ሰርተፍኬት) ማቅረብ አያስፈልገውም፡፡
- በተጠቀሰው መስፈርት በጨረታ የሚሸጠው እቃ በኮሚሽኑ ቁጥጥር ስር ከመግባቱ በፊት ባለቤት የነበረ ወይም የባለቤቱ ወኪል ወይም ቤተሰብ የሆነ ሰው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ አይነትና ብዛት የጨረታ ሰነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) እየከፈሉ ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው (6) ቀን 3፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታው የዕቃዎችን ዝርዝር በያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሀዝና በፊደል ገልፀው እና በተራ ቁጥር 1 ላይ የተገለፁትን በኤንቬሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን 3፡50 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ስድስተኛው ቀን በጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚካሄድ ሲሆን ግልፅ ጨረታው 3:50 ሰዓት ተዘግቶ 4፡00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ሀራጅ ጨረታዉ 4፡30 ሰዓት የሚጀመር ይሆናል።
- ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ-05-ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በመክፈል ንብረቶቹን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ከፍለው የማይወስዱ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ እቃው እንደገና ለጨረታ ይቀርባል፡፡
- ተጫራቾች ለእቃዎች በሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ አሸናፊ ከሆኑ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ 15% (VAT) የሚጨመርበት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን ድረስ ለሽያጭ የተዘጋጁ እቃዎችን በኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ8፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ እና ስድስተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ እቃዎች የሰጡትን የመግዣ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና ለሀራጅ ጨረታ እቃዎች አንድ መቶ ሺህ ብር (100,000) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንከ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 033 551 06 93 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
