የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ልዩ ልዩ የመገጣጠሚያ ፣ ማጠናቀቂያ እቃዎች፣ የኮምባይን ዴስክ ቶፕ እና ሼልፍ አገልግሎት ከነዕቃው አቅርቦት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።
የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ልዩ ልዩ የመገጣጠሚያ ፣ ማጠናቀቂያ እቃዎች፣ የኮምባይን ዴስክ ቶፕ እና ሼልፍ አገልግሎት ከነዕቃው አቅርቦት ግዥ
ግልጽ ጨረታ ቁጥር EMPDE/NCB/01/2017
ድርጅታችን ለፈርኒቸር ምርት ሥራ አገልግሎት የሚውል ፡-
ሎት አንድ ፡- ልዩ ልዩ የመገጣጠሚያ እና ማጠናቀቂያ የፈርኒቸር እቃዎች
ሎት ሁለት፡- የኮምባይን ዴስክ ቶፕ እና ሼልፍ አገልግሎት ከነዕቃው አቅርቦት ግዥ ለመፈጸም ብቃት ያላቸው አምራች፣ አከፋፋይ እና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ነጥቦች ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በዘርፉ ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፤ የታክስ ክሊራንስ ደብዳቤ፤ የተ.እ.ታ ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ ግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና የአቅራቢ ምዝገባ ሰርተፍኬት መሆኑን፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጸውን ሰነድ የማይመለስ ብር 600 /ስድስት መቶ ብር/ በመክፈል ከትም/መሳሪ/ማም/ማከ/ድርጅት ዘወትር በሥራ ሰዓት ጠዋት 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት እንዲሁም ከ7፡30 ሰዓት እስከ 10፡30 ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 35 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ሐምሌ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል፡፡
- ከላይ የተዘረዘሩትንና በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተመለከቱትን ግዴታዎች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የድርጅቱ አድራሻ ፡- ከመገናኛ ወደ ጉርድ ሾላ በሚወስደው መንገድ ከሆሊ ሲቲ ሴንተር ሕንጻ ሲደርሱ ወደ ቀኝ ታጥፎ ይገኛል፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0116 -46-34-81 መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት
