የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የብረታ ብረት እና ተዛማጅ እቃዎች ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብግጨ/ዕቃ/02/11/2017 ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Federal Housing Corporation (የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን)
የጨረታ ማስታወቂያ
ፌ.ቤ.ኮ/ብግጨ/ዕቃ/02/11/2017
- የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የብረታ ብረት እና ተዛማጅ እቃዎች ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብግጨ/ዕቃ/02/11/2017 ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ለኮርፖሬሽኑ አገልግሎት የሚያገለግል የብረታ ብረት እና ተዛማጅ እቃዎች ግዥ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ቴክኒካል ሰነዳቸውንና ዋጋቸውን በተለያዩ በታሸጉ ኤንቨሎፖች ማቅረብ አለባቸው።
|
ተ.ቁ |
የዕቃ ዝርዝር |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
1 |
የብረታ ብረት እና ተዛማጅ እቃዎች |
150,000.00 |
- ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ ሥርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ፈዴራላዊ ዴሞከራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የግዥ መመሪያ መሠረት ሲሆን ከሚፈለገው የብረታ ብረት ተዛማጅ እቃዎች ግዥ ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
- የተሟላ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለገሀር በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 201 ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 30ኛው ወይም ነሐሴ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ በባንክ በተመሰከረለት የባንክ ዋስትና ወይም ሲ.ፒ.ኦ በፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣ ከጨረታ መክፈቻ ዕለትና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ነሐሴ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት የኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክተር 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ
በስልክ ቁጥር- 011-855-53-617 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ዌብሳይት/website:- WWW.agh.gov.et
የፖ.ሣ.ቁ/ P.O.Box:- 299
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
