የኢትዮጵያ አንስቴቲስቶች ማህበር (EAA) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ያሉቤቶች ወይም የቢሮ ቦታዎችን አገልግሎታቸው ለስልጠና እና ጥናት እና ምርምር ማዕከል ሊውል የሚችል ለመግዛት በአካባቢው የሚገኙ ህጋዊ የንብረት ባለቤቶች፤ ግለሰቦች ወይም የንብረት ወኪሎች በተዘጋጀው ጥሪ መሰረት ጨረታ እንዲያቀርቡ ይጋብዛል።
Ethiopian Association of Anesthetists (EAA) (የኢትዮጵያ አንስቴቲስቶች ማህበር)
የስልጠና እና የጥናት ምርምር ማዕከል
ግዢ የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ አንስቴቲስቶች ማህበር (EAA) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ያሉቤቶች ወይም የቢሮ ቦታዎችን አገልግሎታቸው ለስልጠና እና ጥናት እና ምርምር ማዕከል ሊውል የሚችል ለመግዛት በአካባቢው የሚገኙ ህጋዊ የንብረት ባለቤቶች፤ ግለሰቦች ወይም የንብረት ወኪሎች በተዘጋጀው ጥሪ መሰረት ጨረታ እንዲያቀርቡ ይጋብዛል።
መስፈርቶች፡-
- ቦታው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መገኘት አለበት።
- የቦታው ስፋት /መጠን/ ከ100 እስከ 300 ካሬ ሜትር መካከል መሆን አለበት።
- የቦታው ዲጂታል ካርታ በአዲስ አበባ ከተማ መሬት መስተዳድር የተመዘገበ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
- የቤቱ ካርታ በዕዳ ወይም በዋስትና ያልተመዘገ በመሆን አለበት።
- በሀገራችን ህግ እና ደንቦች መሰረት ማንኛውንም የቤት ግብር የከፈለ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
የጨረታ ማቅረብ ዝርዝር፡-
- ተሳታፊዎች የጨረታ ሰነድ ከኢትዮጵያ አንስቴቲስቶች ማህበር ቢሮ በመገኘት መውሰድ ይችላሉ።
- ማህበሩ ባዘጋጀው የመተዳደሪያ ቅፅ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።
- ፍላጎት ያላቸው ተሳታፊዎች ቴክኒካዊ እና ፋይናንስ የጨረታ ሰነዶቻቸውን በፖስታ በማሸግ በኢትዮጵያ አንስቴቲስቶች ማህበር ጽ/ቤት ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ መሰብሰቢያ ሳጥን ወይም ማህበሩ ለዚህ ብሎ ባዘጋጀው የemail አድራሻ vacancy@eaansa.com ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነዶቻቸው በአካል ለሚያቀርቡ በስራ ሰአት ጠዋት 03፡00-6፡00 ከሰአት 8፡00-10፡00 ብቻ ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከውጣበት እለት ጀምሮ ባለው አምስት የስራ ቀናት ብቻ ይሆናል።
- ሰነድ ማስገቢያ በመጨረሻው ቀን እስከ ጠዋቱ 04:00 ሰአት ማስገባት ይኖርባቸዋል; በዚያኑ ዕለት በ 08፡00 ሰአት ላይ የጨረታው ተሳታፊዎች እና የማህበሩ የግዥ ኮሚቴዎች በተገኙበት በማህበሩ ቢሮ ውስጥ ይከፈታል።
የሙያ ማህበሩ አድራሻ፦
- የኢትዮጵያን አንስቴቲስቶች ማህበር (EAA)
- ዲፕሎማት ህንፃ ቢሮ ቁ.204, ሞዛምቢክ መንገድ, ወረዳ 5, ቂርቆስ ክፍለ ከተማ, አዲስ አበባ
- ስልክ ቁጥር 011-1-53-06-01
- Google map / ካርታ - https://maps.app.goo.gl/NZFW7GCDeBMadtKU9 ከሜክሲኮ ወደ ቄራ መንገድ, ከገነት ሆቴል ዝቅ ብሎ (ዲፕሎማት ህንጻ 2ኛ ፎቅ 210)
ማህበሩ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያን አንስቴቲስቶች ማህበር
