Tender Detail

Tender Details

  • Deadline05 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security10.00
  • opening date2025-08-05 00:00:00
  • Categories Vehicle Spare Parts

የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተቀመጡ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


 

የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር LAMC/BD/01-11/2018

 

የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተቀመጡ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መመዘኛዎች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ግሎባል በሚገኘው ከንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ጀርባ ባለው የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ በሚገኘው በፋይናንስ ኮርፖሬት ሰርቪስ መምሪያ በመምጣት የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፣
  2. የተሽከርካሪ መለዎወጫዎቹ የሚገኙበት አድራሻ ሳሪስ አቦ አካባቢ በሚገኘው ከፋፋ የምግብ ኮምፕሌክስ ፋብሪካ አጠገብ ባለው በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ግቢ ነው፡፡
  3. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎቹን በተራ ቁጥር 2 ላይ በተጠቀሰው ቦታ /አድራሻ/ በመሄድ መመልከት ይችላሉ፣
  4. ተጫራቾች የሚገዙትን የተሽከርካሪ መለዎወጫዎች የጨረታ መነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው ሐምሌ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ5፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሑድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፤
  6. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ከፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ይደረጋል፤
  7. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው።
  8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን በ15 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፣
  9. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0942-52-36-99/ 0912-13-47-91 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣
  10.  ኮርፖሬሽኑ በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የዕዳ እና የኃብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን

አዲስ አበባ

 

Save Tender