Tender Detail

Tender Details

  • Company Abay Bank S.C (ዓባይ ባንክ አ.ማ)
  • Address ባምቢስ አካባቢ ኖክ ነዳጅ ማደያ ፊት ለፊት ከሚገኘው ዝቋላ ኮምፕሌክስ ህንፃ 8ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-5-57-17-60
  • Websitehttps://abaybank.com.et/am/
  • Deadline28 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security20000.00
  • opening date2025-07-28 00:00:00
  • Categories Vehicle (Garage Service)

ዓባይ ባንክ አክሲዮን ማህበር ፍላጎት ያላቸውን እና መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በመጋበዝ የተለያዩ ሞዴል ያላቸውን የባንኩን ተሽከርካሪዎች የሰርቪስ እና ጥገና አገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

Abay Bank S.C (ዓባይ ባንክ አ.ማ)


 

የሃገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር፡ ዓባ/ፕፕማ/05/02/2025-26

 

ዓባይ ባንክ አክሲዮን ማህበር ፍላጎት ያላቸውን እና መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በመጋበዝ የተለያዩ ሞዴል ያላቸውን የባንኩን ተሽከርካሪዎች የሰርቪስ እና ጥገና አገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

  1. የዘመኑ የታደስ የንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የግብር መለያ ሰርተፊኬት፣ ታክስ ክሊራንስ፣ የድርጅቱን ፕሮፋይልና ተቋማዊ ብቃት የሚያረጋግጥ መረጃ እንዲሁም የስራ ልምድ እና ሌሎችም ተዛማጅ ዶክመንቶች ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች ከጨረታው በኋላ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 ከማንኛውም ባንክ በተሰራ ሲ.ፒ.ኦ ወይም ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ቢያንስ ለ120 ቀናት የሚቆይ ቅድመ ሁኔታን ባላስቀመጠ የባንክ ዋስትና (ከዓባይ ባንክ የተሰራ የጨረታ ማስከበሪያ አያካትትም) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ለተሽከርካሪዎች ጥገና እና ሰርቪስ አገልግሎት ግዥ የሚያስገቡት ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ (Price Validity Date) መግለፅ አለባቸው። ይህም ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ከ90 ቀን ማነስ የለበትም።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 ብር በዓባይ ባንክ ዓብይ ቅርንጫፍ በመክፈል እና የከፈሉበትን ደረሰኝ በመያዝ ባምቢስ አካባቢ ከሚገኘው ዓባይ ባንክ ዋና መ/ቤት 8ኛ ፎቅ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዲፓርትመንት በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እስከ ሐምሌ 21፣ 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸው።
  6. ጨረታው ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሐምሌ 21፣ 2017 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡30 ዓባይ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ይከፈታል።
  7. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-557-17-60 የባንኩን ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ዲፓርትመንት ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

ዓባይ ባንክ አ.ማ

ዓባይ – የታላቅነት ምንጭ!

 

Save Tender