ዘ ብሩክ ሆስፒታል ፎር አኒማልስ በዚህ ዓመት ለሚያካሂደው ተግባር አጋዥ የሚሆኑ የህክምና መገልገያ መሣሪያዎችንና አላቂ መድሃኒቶችን ከታወቁ የዘርፉ አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
The Brooke Hospital for Animals. (ዘ ብሩክ ሆስፒታል ፎር አኒማልስ)
የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች እና የእንስሳት መድሃኒቶች ግዥ ጨረታ
የጨረታ ቁጥር B-ETH/05/2025
ዘ ብሩክ ሆስፒታል ፎር አኒማልስ በኢፌዲሪ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በቁጥር: 0883 የተመዘገበ መንግስታዊ ያልሆነ ግብረሰናይ ድርጅት ሲሆን ከተመዘገበበት ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ የድርጅቱ አላማ የጋማ እንስሳትን ደህንነትና ጤንነት እንዲጠበቅ ማስቻል ሲሆን ይህንንም ለመተግበር ከመንግስት የእንስሳት ጤና እና የግብርና ኤክስቴንሽን ተቋማት በተጨማሪ ከጅማ፣ ከሀዋሳ፣ ወሎ እና ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ይሠራል፡፡ ድርጅታችን በዚህ ዓመት ለሚያካሂደው ተግባር አጋዥ የሚሆኑ የህክምና መገልገያ መሣሪያዎችንና አላቂ መድሃኒቶችን ከታወቁ የዘርፉ አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በመስኩ የተሠማሩ
-
- ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የተሟላ የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የቤት ቁጥር 797 ከሚገኘው የድርጅታችን ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላው የጨረታ ዋጋቸው 2% በሲፒኦ መልክ ብቻ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በሰም የታሸገውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ከላይ በተ.ቁ. 2 በተጠቀሰው አድራሻ በሚገኘው የብሩክ ጽ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በ15ኛው ቀን ከቀኑ 7፡30 ነው። የጨረታ ማቅረቢያው አስራ አምስተኛ ቀን ቅዳሜና እሁድ፣ ወይም በበዓል ቀናት ከዋለ የጨረታ መዝጊያው ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 7፡30 ይሆናል፡፡ ይሁን እንጂ በተለያዩ አስገዳጅ ምከንያቶች የጨረታ መክፈቻ ቀን ሊራዘም ይችላል።
- ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ውጭ የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በተዘጋበት ቀን በተ.ቁ.4 እንደተመለከተው ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የጨረታ መክፈቻውን ቀን የማራዘም፣ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ እንዲሁም ቀደም ብሎ ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸውን አቅራቢዎች/የጨረታ ተወዳዳሪዎች ከጨረታው የማስወገድ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ድርጅቱ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሱትን የእንስሳት ህክምና መገልገያ መሣሪያዎችንና አላቂ መድሃኒቶችን ዝርዝር ብዛት የቀረበበትን የዋጋ መጠን በማየት ሊቀንስም ሊጨምርም ይችላል፡፡
- ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-661-00-69/011-662-18-85 በመደወል ወይም በኢሜል info@thebrookeethiopia.org አድራሻችን መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻችን፡- 22 ማዞሪያ በአውራሪስ ከቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል በጀርባ ባለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል ወደ 24 በሚወስደው መንገድ ላይ በንጋት ህንፃ እና በአዳነ ገብሩ ህንፃ በኩል ወደ ውስጥ ገባ ብሎ፡፡
ስልክ 011-661-00-69/011-662-18-85
ዘ ብሩክ ሆስፒታል ፎር አኒማልስ
