Tender Detail

Tender Details

  • Company F.D.R.E Authority for civil Society Organization (የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን)
  • Address ቴዎድሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ ኅብረት ኢንሹራንስ ሕንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 608 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-10-20-47-68
  • Websitehttps://acso.gov.et
  • Deadline22 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security20.00
  • opening date2025-07-22 00:00:00
  • Categories Home Appliance And Supplies , Machinery , Metals And Metal Working , Electronics Materials , Used Items , Vehicle Spare Parts

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከተዘጉ ድርጅቶች እና ለፈንድ ድጋፍ ካደረጉ ድርጅቶች ላይ ያገኛቸውን ንብረቶች እነሱም ከጋራጅ የተመለሱ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ ብረታ ብረቶች (ፍሪጅ፣ ኦቭን፣ ድሪል፣ የውሃ ማጣሪያ ፣ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ 

F.D.R.E Authority for civil Society Organization (የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከተዘጉ ድርጅቶች እና ለፈንድ ድጋፍ ካደረጉ ድርጅቶች ላይ ያገኛቸውን ንብረቶች እነሱም ከጋራጅ የተመለሱ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ ብረታ ብረቶች (ፍሪጅ፣ ኦቭን፣ ድሪል፣ የውሃ ማጣሪያ ፣ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ 

  1. ተጫራቾች የጨረታ ሠነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ እየከፈሉ ከተቋሙ ግዥና ፋይናንስ ስራ አስፈጻሚ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 ማስታውቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት የሚችሉ ሲሆን በአስረኛው ቀን ግን የጨረታ ሰነዱ የሚገዛው እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡
  2. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በሚል ስም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከአዲስ አበባ ውጪ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡ አሸናፊዎች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ያሸነፉትን ጠቅላላ ዋጋ ከፍለው ሲመጡ ተመላሽ ይሆናል፤ ለተሸነፉት ተጫራቾች የጨረታ ግምገማ ውጤት በጨረታ አፅዳቂ መፅደቁ ወይም ውድቅ መሆኑ በማስታወቂያ ከተገለጸ በኋላ ሲፒኦ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
  3. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ 10 የስራ ቀናት ሆኖ በ11ኛው ቀን ጨረታው 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 የሚከፈት ይሆናል፡፡
  4. ተጫራቾች ከድርጅቱ የግዥና ፋይናንስ ስራ አስፈፃሚ ክፍል ቢሮ ቁጥር 605 የንብረቶቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ 300 /ሶስት መቶ ብር/ እየከፈሉ በመግዛት ከሰነዱ ላይ ሙሉ ዝርዝሩን ያገኛሉ፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ /ፖስታ/ አዲስ አበባ ከተማ ቴዎድሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ ህብረት ኢንሹራንስ ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 608 በመገኘት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  7. ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጁትን ዕቃዎች በሚገኙበት ቃሊቲ ከአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ አለፍ ብሎ ከአድማስ ዩኒቨርሲቲ አጠገብ በስተቀኝ በሚያስገባው መንገድ 300 ሜትር ገባ ብሎ ኒያላ ኢንሹራንስ የተጎዱ መኪኖች ማቆያ ፊት ለፊት በሚያስገባው መንገድ 200 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው ተቋሙ በተከራየው መጋዘን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 9፡30 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-558 2437/0901-19-09-39 / 09-18-15-61-15

 

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን

 

Save Tender