የደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት ለሁሉም የዞን መምሪያዎችና ተጠሪ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የመኪና እቃ አመታዊ ሎት 2 የመኪና እቃ ፋስት ሙቭ ሎት 3 የመኪና ጎማ ሎት 4 የመኪና ባትሪ እንዲሁም ለ 31 የዞን ሴክተር መ/ቤቶች፣ ለ 22 ወረዳዎች፣ ለ10 ከተማ አስተዳደሮች ለ 9 ክልል ተጠሪ መ/ቤቶች ሎት 5 የከባድ ተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት፣ ሎት 6 የቀላል ተሸከርካሪ ጥገና አገልግሎት ሎት 7 የመድን ዋስትና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሀገር አቀፍ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ግጨ-1-ደወገመ/ግቡ/001/2017
የደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት ለሁሉም የዞን መምሪያዎችና ተጠሪ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የመኪና እቃ አመታዊ ሎት 2 የመኪና እቃ ፋስት ሙቭ ሎት 3 የመኪና ጎማ ሎት 4 የመኪና ባትሪ እንዲሁም ለ 31 የዞን ሴክተር መ/ቤቶች፣ ለ 22 ወረዳዎች፣ ለ10 ከተማ አስተዳደሮች ለ 9 ክልል ተጠሪ መ/ቤቶች ሎት 5 የከባድ ተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት፣ ሎት 6 የቀላል ተሸከርካሪ ጥገና አገልግሎት ሎት 7 የመድን ዋስትና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin/ ያላቸው
- የግዥ መጠኑ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፤
- ለተሽካርካሪ ጥገና ግዥ በዘርፉ የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ያለው ሆኖ ደረጃ 2 ወይም ደረጃ 3 ወይም ደረጃ 4 መሆናቸውን የሚገልፅ ሰርተፊኬት ያላቸው
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
- በከባድና ቀላል ተሽከርካሪ ጥገና በጨረታው የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች በአማራ ክልል ደሴ ከተማ እና ኮምቦልቻ ከተማ ላይ ብቻ በጨረታ የሚያሸንፍባቸውን ተሽከርካሪዎች የጥገና አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የጥገና ተቋም ያላቸው መሆን አለበት፡፡
- የመድን ሽፋን አገልግሎት ግዥ በጨረታ የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች በአማራ ክልል ደሴ ከተማ ላይ ብቻ አገልግሎቱን የሚሰጥ ቅርንጫፍ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች አርጅናል እቃ መሙላትና ያሸነፉባቸውን እቃዎች በባለሙያ ማስፈተሽና ማረጋገጥ አለባቸው
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን / ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፤
- ማንኛውም ተጫራች በሰነዱ ላይ ዋጋ ሲሞሉ ከእያንዳንዱ የእቃ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ መሙላት አለባቸው፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 601 ማግኘት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር የእቃውን ወይም የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ ለሎት 1 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር፣ ለሎት 2 ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ለሎት 3 140,000.00 (አንድ መቶ አርባ ሺህ) ለሎት 4 ብር 20,000̃0 (ሀያ ሺህ) ለሎት 5 ብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ ብር) ለሎት 6 ብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ ብር) ለሎት 7 ብር 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ ብር) በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ እንደተጫራቹ ምርጫ ሲፒኦ /CPO/ ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (ከ60 ቀን ያላነሰ) ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ ሲያሲይዙ በመምሪያው የገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ኮፒው ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት ከተሽከርካሪ ጥገና ውጭ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል ነገር ግን ለተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት ግዥ 3% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል።
- ውድድሩ የሚካሄደው የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት በየደረጃቸው እና በየጥገናው አይነት በሎት ጠቅላላ ድምር ነው። የመኪና እቃዎቹ በመኪና ሞዴላቸው በሎት ጠቅላላ ድምር ሲሆን የመኪና ባትሪውም በተናጠል ዋጋ ውድድሩ የሚካሄድ ሲሆን የመድን ሽፋን አገልግሎት ግዥም በጠቅላላ ድምር በሎት ሲሆን የመኪና ጎማው በነጠላ ዋጋ ውድድሩ ይካሄዳል ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 610 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን መግዛትና በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 610 በ16ኛው ቀን ከጧቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን የስራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጧቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ 4:30 ላይ ይከፈታል፡፡
- በጨረታው ለማሳተፍ ለሚፈልጉ እቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 610 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 111 81 18 /19 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፉትን እቃ ደቡብ ወሎ ዞን ባሉ 3 የፑል ንብረት ክፍሎች ገቢ ማድረግ አለባቸው።
- በውድድር ወቅት የተጋነነ ዋጋ ከተገኘ ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበር ኦርጅናል መሆኑን ካስያዙት ባንክ ማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ድምር ካላስቀመጡ ከውድድር ውጭ ይደረጋሉ።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ ሙብቱ የተጠበቀ ነው።
- የመኪና ባትሪ እና የመኪና ጎማው ሳምፕል ስለተቀመጠ የጨረታ ሰነድ ስትገዙ ሳምፕሉን ይመልከቱ።
የደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ
