Tender Detail

Tender Details

  • Company አምቦ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-236-33-99
  • Website
  • Deadline26 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security5.00
  • opening date2025-07-26 00:00:00
  • Categories Food And Beverage , Merchandise

የአምቦ የገ/ህ/ሥራ ዩኒየን ከአባላቱ ገዝቶ በአምቦ እና በቡራዩ ታጠቅ ማዕከላዊ መጋዘን ያከማቸውን በቆሎ ብዛቱ 10000 (+or-) ኩንታልና ነጭ ገብስ ብዛቱ 400 ኩንታል አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

አምቦ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን


 

የጨረታ ማስታወቂያ

ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የእህል ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የአምቦ የገ/ህ/ሥራ ዩኒየን ከአባላቱ ገዝቶ በአምቦ እና በቡራዩ ታጠቅ ማዕከላዊ መጋዘን ያከማቸውን በቆሎ ብዛቱ 10000 (+or-) ኩንታልና ነጭ ገብስ ብዛቱ 400 ኩንታል አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ተጫራቾቹ ማሟላት ያለባቸው ነገሮች፡-

  1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ከዩኒየኑ ገበያ ክፍል በ500 ብር መግዛት ይችላሉ።
  2. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው እና የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆኑን መረጃ ማቅረብ የሚችል፤
  3. ተጫራቾች የበቆሎውን ሁኔታ በአምቦ እና በቡራዩ ታጠቅ በዩኒየኑ መጋዘን ገብሱን አምቦ ባለው የዩኒየኑ መጋዘን በስራ ሰዓት ተገኝተው ማየት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ በቅድሚያ 5% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡ ጨረታው እንዳበቃ ለተሸናፊዎች ሲመለስላቸው አሸናፊዎች ከግዥ ውስጥ የሚታሰብላቸው ይሆናል።
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ጠዋት ታሽጎ በዚያኑ ቀን ጠዋት 5፡00 ሰዓት ላይ አምቦ ባለው በዩኒየኑ ቢሮ ይከፈታል: ፡ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  6. ተጫራቾች/ተወካዮቻቸው በጨረታው መክፈቻ ላይ ለመገኘት ከድርጅታቸው የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተወዳዳሪዎች በሙሉ ባይገኙም በተገኙ ተጫራቾች ፊት ጨረታው በዕለቱ ይከፈታል።
  7. ተጫራቾች የመግዣ ዋጋቸውንና ለጨረታው የተጠየቁትን መረጃዎች በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. የጨረታው አሸናፊ በገባው ውል መሰረት ክፍያ አጠናቀው ካሸነፉበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊው በተሰጠው ቀናት ውስጥ ያላነሳ እንደሆነ ያስያዘው ገንዘብ የማይመለስለት ከመሆኑም በላይ በየቀኑ ለእያንዳንዱ ኩንታል የመጋዘን ኪራይ ብር 0.5ሳ ይከፍላል።
  9. አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም።
  10. ጨረታውን ያሸነፈ አሸናፊ ለውል ማስከበሪያ የጠቅላላውን ዋጋ 10% የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርበታል።
  11. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ 0913 379 435፣ 0112 363 399 ይጠቀሙ።

 

አምቦ የገ/ህ/ሥራ ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ

 

 

Save Tender