Tender Detail

Tender Details

  • Company Abay Bank S.C (ዓባይ ባንክ አ.ማ)
  • Address ባምቢስ አካባቢ ኖክ ነዳጅ ማደያ ፊት ለፊት ከሚገኘው ዝቋላ ኮምፕሌክስ ህንፃ 8ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-5-57-17-60
  • Websitehttps://abaybank.com.et/am/
  • Deadline21 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security2.00
  • opening date2025-07-21 00:00:00
  • Categories Banking Equipment And Services

ዓባይ ባንክ አ.ማ ከቅርንጫፎች ላይ የተነሱ ካውተሮች እና ኬጅ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

Abay Bank S.C (ዓባይ ባንክ አ.ማ)


                   

    ዓባይ ባንክ አ.ማ

ያገለገሉ የካውተር እና ኬጅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር ዓባይ 04/2017

 

ዓባይ ባንክ አ.ማ ከቅርንጫፎች ላይ የተነሱ ካውተሮች እና ኬጅ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

 

ተ.ቁ

የዕቃው ዓይነት

ጨረታው የሚዘጋበት ቀን

ጨረታው የሚከፈትበት ቀን

 

1

ከ34 ቅርንጫፎች የተነሱ ካውተሮች ሲሆኑ ከዚህ ውስጥ 31 የሚሆኑት ካውተሮች ከካውተሩ በተጨማሪ የካውተሩ የላይኛው ክፍል /TOP/ እምነበረድ፤ ኬጅ የተሰራበት አልሙኒየም እና መስታወትን ያካተተ ሲሆን ቀሪው ሶስቱ ግን ካውተር ብቻ ያላቸው ናቸው።

 

ሐምሌ 14 ከቀኑ 8፡30

 

ሐምሌ 14 ከቀኑ 9፡00

 

  1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በዓባይ ባንክ ዓብይ ቅርንጫፍ በመክፈልና ደረሰኙን በመያዝ ባምቢስ ኖክ ማደያ ፊት ለፊት በሚገኘው ዝቋላ ኮምፕሌክስ 8ኛ ፎቅ ከግዥና ንብረት አስተዳደር ዲፖርትመንት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት 2፡00-6፡00፤ ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት 2፡00-6፡00 ማግኘት ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች ካውተሮቹ በሚገኝበት አድራሻ ዓባይ ባንክ ዋና/ቤት እና ቃሊቲ ማሰልጠኛ በሚገኘው የባንኩ መጋዘን የሚገኝ ሲሆን ተጫራቾች ቦታው ድረስ በመቅረብ ጨረታው ከሚዘጋበት ቀን በፊት ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ቦታው ድረስ ሄደው መመልከት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱትን የካውተር እና ኬጅ የሚገዙበት ዋጋ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤቨሎፕ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ በባንኩ ዋናው መ/ቤት ባምቢስ ኖክ ማደያ ፊት ለፊት ዝቋላ ኮምፕሌክስ 8ኛ ፎቅ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዲፖርትመንት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  4. ጨረታው ሐምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 9፡00 ሰዓት በተጫራቾች ወይም ተወካዮች በተገኙበት ይከፈታል።
  5. ተጫራቾች ለጨረታ የሚያስገቡት የአጠቃላይ ዋጋ 2% በባንክ ክፍያ ማዘዣ (C.P.O) ለጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች የሚጫረቱትን ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% ጨምሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።  

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251-115571529/+251-115549741 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።

 

“ዓባይ-የታላቅነት ምንጭ!!”

 

Save Tender