Tender Detail

Tender Details

  • Company South Radio and Television Agency (የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት)
  • Address ሀዋሳ ከተማ : ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046 212 5541
  • Websitehttps://srta.gov.et/
  • Deadline23 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security20000.00
  • opening date2025-07-24 00:00:00
  • Categories Vehicle (Garage Service)

የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በመ/ቤቱ የሚገለገልባቸውን ተሽከርካሪዎች በማስጠገን በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ ጋራዦችን በጨረታ በማወዳደር ለአንድ ዓመት የሚቆይ የጥገና የእጅ ዋጋ ደንበኛ ለመያዝ ይፈልጋል።

South Radio and Television Agency (የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት)


 

በድጋሚ የወጣ የተሽከርካሪ ጥገና የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 003/2017

 

የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በመ/ቤቱ የሚገለገልባቸውን ተሽከርካሪዎች በማስጠገን በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ ጋራዦችን በጨረታ በማወዳደር ለአንድ ዓመት የሚቆይ የጥገና የእጅ ዋጋ ደንበኛ ለመያዝ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው በመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች፡-

  1. ተጫራቾች በሥራ መስኩ የተሰማሩና የተሽከርካሪ ጥገና ጋራዥ የብቃት ማረጋገጫ ለቀላል ሁለገብ ጥገና እንዲሁም ለመካከለኛና ለከባድ ተሽከርካሪ ጥገና 3ኛ ደረጃ እና ከዚያ በላይ ደረጃ ያገኙና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች በሀገር ውስጥ አገልግሎት ሰጪዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የተሰጠ ማስረጃ፣ በሥራ መስኩ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ፣ የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸውና በጨረታ ላይ እንዲሳተፉ የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (guaranty) ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኮፒ በመያዝ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ወደ ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት (ቢሮ ቁጥር 10) ቀርበው የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት (ቢሮ ቁጥር 11) የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቴክኒካልና ፋይናሻል ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ሁለቱንም በአንድ እናት በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ውስጥ በማድረግ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ድረስ በዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው በ16ኛው የስራ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጠዋት 3፡00 ሰዓት ታሽጎ 3:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  7. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ 046 212 5541/ 046 220 4750/ 046 220 1091 ደውሉ መጠየቅ ይቻላል።

 

የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት

 

Save Tender