ኢምፓክት ኢንሸቲቭስ የተባለ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ሲገለገልበት የነበረን የታርጋ ቁጥሩ 35-4376 የሆነ አንድ ያገለገለ የመስክ ተሽከርካሪ ባለበት ሁኔታ በብር 2,250,000.00 (ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) መነሻ ዋጋ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
IMPACT INITIATIVES (ኢምፓክት ኢንሸቲቭስ)
የጨረታ ማስታወቂያ
ኢምፓክት ኢንሸቲቭስ የተባለ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ሲገለገልበት የነበረን የታርጋ ቁጥሩ 35-4376 የሆነ አንድ ያገለገለ የመስክ ተሽከርካሪ ባለበት ሁኔታ በብር 2,250,000.00 (ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) መነሻ ዋጋ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
1ኛ. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 (ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ ገርጂ መብራት ሃይል ኦልማርት ሱፐርማርኬት ዝቅ ብሎ ከሚገኘው ማግ ኢንተርናሽናል ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 206 ድረስ በመቅረብ ከድርጅቱ ግዢና ፋይናንስ ቢሮ የንብረቱን ዝርዝር መረጃ የያዘውን የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ እየከፈሉ መግዛት ይችላሉ፡፡
2ኛ. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የገዙትን የጨረታ ሰነድ በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 (ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ንበረቱ በሚገኝበት አድራሻ ማለትም በአዲስ አበባ ከተማ ገርጂ መብራት ሀይል ህንጻ ፊት ለፊት በሚገኘው የቀድሞ የካቲት ወረቀት ፋብሪካ ጎን ባለው ክፍት ቦታ ከ4፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በመቅረብ ንብረቱን መመልከት ይችላሉ፡፡
3ኛ. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ጠቅላላ ዋጋ 20% (20 በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማሰራት አለባቸው፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ዋስትና ሲፒኦ (CPO) ጨረታውን ላሸነፈው ወገን ከሚከፍለው ጠቅላላ ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል፡፡
4ኛ. ተጫራቾች የንብረቱን ዝርዝር በያዘው ሰነድ ውስጥ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ (Column) ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለስርዝና ድልዝ ገልፀው ማስፈር ተጫራቹን ወይም ሕጋዊ ወኪሉን ሙሉ ስም ማስፈርና ቅጹ የሚጠይቀውን ሁሉ በትክክል መሙላትና መፈረም ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝና ድልዝ ካለ ከጎኑ የተጫራቹ ሙሉ ስምና ፊርማ ከማስተካከያው ጎን መስፈር አለበት፡፡
5ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 (ሰባት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከ04፡00-10፡00 ሰዓት (ከአራት እስከ አስር ሰዓት) ባለው ጊዜ ውስጥ የጨረታውን የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ካሰሩት የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ማረጋገጫ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) እና የተጫራቹን ወይም ሕጋዊ ወኪሉን መታወቂያ ኮፒ ጋር በማያያዝ በኤንቨሎፕ በማሸግ በአዲስ አበባ ከተማ ገርጂ መብራት ኃይል ኦልማርት ሱፐርማርኬት ዝቅ ብሎ ከሚገኘው ማግ ኢንተርናሽናል ህንጻ 2ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 206 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
6ኛ. የጨረታ ሳጥኑ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 (ሰባት) ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በሰባተኛው ቀን በ4፡30 (አራት ተኩል) ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያው ቀን በ05፡00 (አምስት) ሰዓት ላይ ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙብት በአዲስ አበባ ከተማ ገርጂ መብራት ሃይል ኦልማርት ሱፐርማርኬት ዝቅ ብሎ ከሚገኘው ማግ ኢንተርናሽናል ህንጻ 2ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 206 ውስጥ ይከፈታል፡፡
7ኛ. አሸናፊው ተጫራች ጨረታውን ማሸነፉ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ3 (በሶስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ዋጋ ሙሉ በሙሉ ገቢ ማድረግ አለበት፤ ንብረቱንም በ5 (በአምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የመረከብ ግዴታ አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ያስያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
8ኛ. ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 09-11-63-62-65 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ኢምፓክት ኢኒሸቲቭስ
