በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፤ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ ተሸከርካሪዎችን በሀራጅ ጨረታ እንዲሁም የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን ፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
AA Kaliti Customs Office (አ.አ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት)
በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተያዙና የተወረሱ ተሽከርካሪዎች እና ልዩ ልዩ
ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 50/2017
በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፤ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ ተሸከርካሪዎችን በሀራጅ ጨረታ እንዲሁም የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን ፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች በቅጹ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃ ተዘጋጅቶ ከሀሙስ ሐምሌ 03/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በመሆኑም
- በተሸከርካሪ ሀራጅ ጨረታ ለመሣተፍ ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (C.P.O) ጨረታው ከመጀመሩ አስቀድሞ ማስያዝና ማስመዝገብ ይኖርበታል፡፡
- በግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (C.P.O) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኢንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርበት ሲሆን ለሃራጅ ጨረታ ደግሞ ከጨረታ አንድ ቀን በፊት ይዞ ማስመዝገብ ይኖርበታል፡፡
- በጨረታው ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች የተሽከርካሪውን እና የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሀሙስ ሐምሌ 03/2017 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- በዕቃ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በቅ/ፅ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የተሽከርካሪ ሀራጅ ጨረታ ለመሳተፍ ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ተሸከርካሪዎች ብር 100,000.00 እና የዕቃ ሐራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ለዕቃዎች ብር 100,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በተ.ቁ 5 በተገለጸው አድራሻ ተጫራቹ ማስያዝ አለበት፡፡ ነገር ግን በዕቃ ሐራጅ በጨረታ ሰነድ ላይ በሚገለጹ የተወሰኑ ዕቃዎች ላይ የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) መጠን የሚወሰን መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ፡፡
|
ተ.ቁ |
የቅ/ጽ/ቤቱ ስም |
የጨረታው አይነት |
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነዱ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት |
የእቃ ሀራጅ |
እስከ 07/11/2017 |
08/11/2017 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል። |
|
የእቃ ግልፅ |
እስከ 08/11/2017 |
09/11/2017 3፡45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል። |
||
|
የተሽከርካሪ ሀራጅ |
እስከ 09/11/2017 |
10/11/2017 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል። |
- የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- አአ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡
- ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ በተ/ቁ 10 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- አዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ - 011- 470 - 85-03
አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ ያለበት አዲሱ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ
በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
