የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ በክልሉ ስር ለሚገኙ ጤና ተቋማት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ የሳኒቴሽን ዕቃዎች እና የልብስ ስፌት ማሽን በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
Amhara Health Bureau (የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ በክልሉ ስር ለሚገኙ ጤና ተቋማት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ የሳኒቴሽን ዕቃዎች እና የልብስ ስፌት ማሽን በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ለመወዳደር የተጋበዙ መሆኑን እያሳወቅን፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ሰርተፊኬት/ የሚያቀርቡ፡፡
- ከላይ በተራ ቁ 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሚገዛው ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ ከ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነና የቫት ሰርተፊኬት ኮፒ ማስያዝ አለበት፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩት ጠቅላላ ዋጋ ብር 2% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የሚያስይዝ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ በጊዜያዊነት በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 2017 ዓ.ም በ 8:30 ሰዓት ታሽጎ 9፡00 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በተከታዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል፡፡
- በሌላ መልኩ ሁሉም በጨረታው የተጋበዙ ተወዳዳሪዎች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ሞልተው ከጨረታ መክፈቻው ጊዜ በፊት ከመለሱ እና ከተረጋገጠ የሰነድ መከፈቻው ቀን ሳይጠበቅ የተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ እንዲከፈት ይደረጋል፡፡
- ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ቢሮው የግዥውን መጠን አስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጭ አብክመ ጤና ቢሮ መጋዘን ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
- በጨረታው የተጋበዘ ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ 11፡30 እና በ16ኛው ቀን እስከ 8፡30 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከቢሮው ግዥ ባለሙያዎች እጅ መውሰድ ይችላል ፡፡
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ስለ ጨረታው መረጃ ከፈለጉ አብክመ ጤና ቢሮ ስልክ ቁጥር 058-222-1127 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ
