አጋርፋ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ በ2015/2016/2017 የምርት ዘመን ያመረተውን 1165 ኩንታል የጎመን ዘር፣ 100 ኩ/ል ትራቭለር ገብስ፣ 2350 ኩ/ል አዶሻ ገብስ፣ 1460 ኩንታል ኪንግ በርድ ስንዴ እና 1ኛ ደረጃ ዛላ በርበሬ 5.3 ኩ/ል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
Agarfa Agricultural Technical Vocational Educational & Training College (አጋርፋ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ)
የምርት ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የሽያጭ መለያ ቁጥር 08/002/2017 አጋርፋ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ በ2015/2016/2017 የምርት ዘመን ያመረተውን 1165 ኩንታል የጎመን ዘር፣ 100 ኩ/ል ትራቭለር ገብስ፣ 2350 ኩ/ል አዶሻ ገብስ፣ 1460 ኩንታል ኪንግ በርድ ስንዴ እና 1ኛ ደረጃ ዛላ በርበሬ 5.3 ኩ/ል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጹትን መመሪያዎች እና ግዴታዎችን በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ
- ከመስኩ ጋር አግባብነት ያለውና የታደሰ /የእድሳት ጊዜው ያላለፈበት የሥራ ንግድ ፍቃድ።
- የግብር ክፍያ ክሊራንስ የምስክር ወረቀት።
- ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ምርት የሰጠውን ጠቅ/ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ እና የዋስትና ጊዜው ከ2 (ሁለት) ወር ያላነሰ የባንክ ዋስትና /CPO/ በኮሌጁ በአጋርፋ የግብርና ቴክኒክ ሙያ ትምህርት ሥልጠና ኮሌጅ ስም በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለፀለት በ10 ቀናት ውስጥ የውል ስምምነት ካልፈጸመ ፍቃደኛ እንዳልሆነ ተቆጥሮ ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለኮሌጁ ገቢ ይሆናል።
- የተዘጋጀውን የመጫረቻ ሰነድ ከአጋርፋ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ ኮሌጅ ከግዢና ፋይናንስ ሥራ አስፈጻሚ ቢሮ እና አዲስ አበባ ኃይሌ ገ/ሥላሴ ጎዳና በጌታነህ በሻህ ህንጻ በኩል ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ አዲስ ህይወት ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘዉ አላጌ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ ኮሌጅ ጉዳይ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ከሚገኘው የአጋርፋ ኮሌጅ ጉዳይ አስፈጻሚ ጽ/ቤት በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 500 (አምስት መቶ ብር) በሥራ ቀናት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ቀናት እስከ መዝጊያው ቀን ድረስ መግዛት ይቻላሉ እንዲሁም የዋጋ ማቅረቢያቸውን ኦሪጂናሉንና ኮፒውን በመለየት አስፈላጊ ከሆኑ ከተያያዘ የጨረታ ሰነዶች ጋር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ከፍ ብሎ በተጠቀሰው አድራሻ አዲስ አበባ የኮሌጁ ጉዳይ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው መዝጊያው ቀን እና የሚከፈትበት ቀን በጨረታ ስነድ ላይ የሚገለጽ ሲሆን ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በኮሌጁ ጉዳይ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል።
- የጨረታ መክፈቻ ቀን እንደ አጋጣሚ ሆኖ በሕዝባዊ ብሔራዊ በዓል ላይ የሚውል ከሆነ ጨረታው በቀጣይ የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይከፈታል።
- ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት ተቀባይነት የለውም /አይቻልም/።
- የምርቱን ናሙና ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች አዲስ አበባ ላይ የጨረታውን ሰነድ ከገዙበት የኮሌጁ ጉዳይ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ወይም አርፋ የግብርና ቴ/ሙ/ሥ ኮሌጅ አጋርፋ ባሌ ቀርበው ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ በቢሮ ቁጥር 20 የገበያ ልማትና ሽያጭ ዴስክ ማየት ይችላሉ።
- ኮሌጁ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011 662 5004 አዲስ አበባ /09 11 49 08 70/ 09 30 10 80 07 ወይም 09 22 31 92 74 በአጋርፋ ኮሌጅ የገበያ ልማት ሽያጭ ዴስክ ላይ መጠቀም ይችላሉ።
አጋርፋ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ
