Tender Detail

Tender Details

  • Company የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
  • Address ድሬዳዋ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 025-112-74-51
  • Website
  • Deadline18 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-18 00:00:00
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከሚያስተዳድራቸው ነባር ቤቶች መካከል ለመኖሪያ ወይም ለንግድ አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉ 2 ቤቶችን በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/ሽ/002/2017 አወዳድሮ በሽያጭ ለማስተላለፍ ይፈልጋል።

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


 

የቤት ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር፡- ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/ሽ/002/2017

 

  1. የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከሚያስተዳድራቸው ነባር ቤቶች መካከል ለመኖሪያ ወይም ለንግድ አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉ 2 ቤቶችን በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/ሽ/002/2017 አወዳድሮ በሽያጭ ለማስተላለፍ ይፈልጋል።
  2. ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውነው የቤቶች ሽያጭ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና የመወዳደሪያ ተመን ዋጋ በአንድ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።
  3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን መመሪያ መሰረት ነው።
  4. የተሟላ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ከሰኔ 25 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የተወዳደሩባቸውን የቤቶች ዝርዝር ሁኔታ በዚህ ሰነድ በክፍል 3 ተያይዞ በሚገኘው የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ/ቅጽ ሞልተውና ተፈላጊ ሰነዶችን በማካተት በዚህ ሰነድ ላይ ተያይዞ በክፍል 2 ከቀረበው የተጫራቾች መመሪያ/ ግዴታ መሠረት በተዘጋጁት የጨረታ ሳጥኖች ከዚራ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አዳራሽ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን ከዚራ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አዳራሽ ብቻ ማስገባት ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ወይም በድሬዳዋ ከተማ በማስታወቂያ ቦርድ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ወይም ሐምሌ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ቀን ከሰዓት 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ሲ.ፒ.ኦ በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታው መክፈቻ ዕለትና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ሰነዱ ክፍል 1 ላይ በተገለፀው ቀንና ሰዓት ይከፈታል። የጨረታ ሰነዱ ሽያጩም በኮርፖሬሽኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሚከናወን ይሆናል።
  7. ተጫራቾች ቤቶቹን በአካል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ማብቂያው ቀን ድረስ በስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት በቅርንጫፍ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ለዚሁ ስራ በሚመደቡ ባለሙያዎች እና በሚወጣው ፕሮግራም መሰረት ቤቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ቤቶቹን መመልከት ይችላሉ።
  8. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፡- 025-112-74-51 እና 09-21-85-25-80 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

 

Save Tender