ድርጅታችን ሐበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበር ሆለታ ከተማ አካባቢ ለሚገኘው ፋብሪካው የምርት ሂደት የሚረዳ ዶዘር ማሽን ከስድስት ወር እና ከዛ በላይ በኪራይ ለማሰራት ይፈልጋል።
Procurement Bid No.01/ የቡልዶዘር ኪራይ
ጨረታ 2017/
ለፋብሪካ ስራ የሚውል የቡልዶዘር ማሽን ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ሐበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበር ሆለታ ከተማ አካባቢ ለሚገኘው ፋብሪካው የምርት ሂደት የሚረዳ ዶዘር ማሽን ከስድስት ወር እና ከዛ በላይ በኪራይ ለማሰራት ይፈልጋል። ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለፀውን የማሽኑ ዝርዝር መረጃ/ስፔስፍኬሽን መሰረት ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው ተጫራቾች በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።
|
የማሽኑ አይነት |
ቡልዶዘር |
|
ብራንድ |
CAT |
|
ሞዴል |
D8R |
|
የተመረተበት ሀገር |
USA |
|
የጎን ስፋቱ |
3.05ሜ |
|
እርዝመት |
6.91ሜ |
|
ቁመት |
3.51ሜ |
|
የሲሊንደር ብዛት |
6 |
|
የሚሰራበት ነዳጅ አይነት |
ናፍጣ |
|
የፈረስ ጉልበቱ |
305 HP |
|
የኪራይ ጊዜ |
ከስድስት ወር ጀምሮ |
- ተጫራቾች ህጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የፈቃዳቸውን ኮፒ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆቸው ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በጨረታው ላይ ወይም በሚሰጠው አገልግሎት ላይ ጥያቄ ካላቸው ወይም ማብራሪያ የሚፈልጉ ከሆነ ከጨረታ ማስገቢያው ሶስት ቀናት በፊት በጽሑፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከተገለጸው የጊዜ ገደብ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም ጥያቄ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ቫትን ጨምሮ መሆኑን በግልፅ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
ተጫራቾች ከላይ በተገለፀው መስፈርት መሰረት የኪራይ አገልግሎት ለመስጠት የሚያቀርቡትን ዋጋ በፖስታ አሽገው ግዢ እና አቅርቦት ክፍል እስከ ሐምሌ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን እያሳወቅን ተወዳዳሪዎች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ከላይ እስከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ድረስ ብቻ ከታች በተመለከተው አድራሻ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ኩባንያው የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡ አሮጌው ቄራ ከንግድ ማተሚያ ቤት ጀርባ ጌት-አስ ኢንተርናሽናል ሕንፃ 7ኛ ፎቅ
ስልከ: 0944122311/0912850906
ሐበሻ ሲሚንቶ አ.ማ
