Tender Detail

Tender Details

  • Deadline15 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price100.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-15 00:00:00
  • Categories Materials , Kitchen Materials

የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ለምግብ ቤት አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 010/17

 

የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ለምግብ ቤት አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚወዳደሩ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው። በዚህም መሰረት ለግብር ዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ ክሊራንስ ወይም በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ተፈላጊ ሰነዶች ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀን ሲሆን ሰነድ የሚሸጠው በስራ ሰአት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር/ አዲስ አባባ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 ሽያጭ ክፍል በመክፈል ደረሰኝ ይዘው ቢሮ ቁጥር 208 አቅርቦትና ኮንትራት አስተዳደር ቡድን ቢሮ በመምጣት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡

የጨረታ ፖስታውን ፋይናንሻል እና ቅድመ መገምገሚያዎችን /ቴክኒካል ሰነድ/ በተለያየ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት አሽጎ ማቅረብ አለባቸው።

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የጨረታ ሰነድ ላይ /የተገለፀውን ብር በሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና ከቴክኒካል /ህጋዊ ሰነዶች/ ኦርጅናል ሰነድ ጋር ወይም ለብቻው በፖስታ አሽጎ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀን ክፍት ሆኖ በ15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከ8:30 ጀምሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡

ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን እንዳስፈላጊቱ በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ስልክ ቁጥር 0116-454147/0116-453598 /0118-694931 ከሳህሊተ ምህረት ማርያም ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት የሚገኘው ህንፃ

 

የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት

 

Save Tender