በአድማስ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኝ ፒክአፕ ደብል ገቢና ሞዴል L.N-106 1995 ስሪት የሆነ መኪና በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
አድማስ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 4138/2017
በአድማስ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኝ ፒክአፕ ደብል ገቢና ሞዴል L.N-106 1995 ስሪት የሆነ መኪና በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች/ግለሰብ ወይም ድርጅት የጨረታ ሰነዱ የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በአድማስ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒዬን ፋይናንስ ክፍል በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ ሰነዱ የሚሸጠው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ይሆናል፡፡
- የመኪናውን ሁኔታ ይህ የሽያጭ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአካል ተገኝቶ ማየት ይቻላል፡፡
- የጨረታ ሽያጩ ማስታወቂያ በወጣበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጐ በዛው ዕለት 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 በአድማስ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ስም በሲ.ፒ.ኦ፣ ካሽ እና ቢድቦንድ የጨረታ ሽያጭ ሳጥኑ ከመታሸጉ በፊት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ዋጋ የጨረታ ውጤት በሚመለከተው አካል ፀድቆ በማስታወቂያ እንዲከፈል በተነገራቸው በ1 ዙር ከፍለው ማጠናቀቅ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ በመንተራስ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ ግለሰብ አሸናፊነቱ በሚመለከተው አካል መፅደቁ በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ክፍያ በመፈፀም መኪናውን ተረክቦ በተረከበ በ5 ቀናት ውስጥ ወጪ ማድረግ አለበት፡፡
- በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ ሽያጭ አሸናፊው በሚመለከተው አካል መጽደቁ ለአሸናፊ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ የሚመለስላቸው ይሆናል፡፡
- ዩኒየኑ በሽያጩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ የሽያጭ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- የጨረታ ማስከበሪያ ቢድቦንድ ለምታቀርቡ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ማስከበሪያ የቆይታ ጊዜ ከ60 ቀን ማነስ የለበትም፡፡
በሌላ በኩል መኪናው የተወሰነ ግጭት ያለውና ተነድቶ ወደ ወልቂጤ ከተማ የሚገኘው የአድማስ ግቢ የመጣ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0113301519 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድማስ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን
