Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የውጊያ ቴክኒክ ት/ቤት
  • Address እንጦጦ (መከላከያ ውጊያ ምህንድስና ኮሌጅ እንጦጦ ቅጥር ግቢ ውስጥ)፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0335400612/092484626
  • Website
  • Deadline09 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-09 00:00:00
  • Categories Transportation Service And Cargo

በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት ባለው በጀት 1ኛ ለት/ቤቱ ሰራዊት አባላትና ሲቪል ሰራተኞች አውቶቢስ (ደረጃ1) ሰርቪስ አገልግሎት፤ 2ኛ ለት/ቤቱ ከፍተኛ መኮንኞች የሃይሩፍ (ደረጃ 1) ሰርቪስ አገልግሎት ኪራይ በጨረታ ሰነዱ ክፍል 6 ላይ በተገለፁት መሠረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የውጊያ ቴክኒክ ት/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር፡- ው/ቴ/ት/ቤት ግ/ጨ 001/2018

 

በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት ባለው በጀት 1ኛ ለት/ቤቱ ሰራዊት አባላትና ሲቪል ሰራተኞች አውቶቢስ (ደረጃ1) ሰርቪስ አገልግሎት፤ 2ኛ ለት/ቤቱ ከፍተኛ መኮንኞች የሃይሩፍ (ደረጃ 1) ሰርቪስ አገልግሎት ኪራይ በጨረታ ሰነዱ ክፍል 6 ላይ በተገለፁት መሠረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማናቸውም ተጫራቾች፡-

  1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የአቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ ስለ ግብር አከፋፈል የሚሰጥ ማስረጃ፤ ለተጨማሪ እሴት ታክስ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ፤ ተያያዥነት ያላቸው ማስረጃዎች ለአውቶቢስ ሰርቪስ አገልግሎት ሙሉ ኢንሹራንስና የ3ኛ ወገን ኢንሹራንስ ኮፒ እና የተሽከርካሪዎችን የቴክኒክ ፍተሻ ብቃት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የተሟሉ በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጁ የጨረታ ሰነዶችን ከዚህ በታች በቁጥር 6/ሐ/ በተገለፀው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  3. በቁጥር 6 “ለ” በተገለፀው አድራሻ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን 23/10/2017 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ 10ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት ድረስ የመጫረቻ ሰነዳቸውን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም በጨረታ ሰነዱ ክፍል 6 ላይ በሒሳብ መደብ 6252 (የአውቶቢስ ሰርቪስ አገልግሎት) የሚካፈሉ ተጫራቾች ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)፤ በሒሳብ መደብ 6252 (ለሃይሩፍ ሰርቪስ አገልግሎት) የሚካፈሉ ተጫራቾች ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ከታወቀ ባንክ ሲፒኦ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቁጥር 6 “መ” በተገለፀው አድራሻ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ (ተከታታይ ቀናት ተቆጥረው) በ10ኛው ቀን በ9፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  4. የአውቶቢስ ሰርቪስ አገልግሎቶች የሚሰጡት አዋሽ አርባ ከተማ (አፋር ክልል ከአዲስ አበባ 240 ኪ/ሜ) የሚገኘው የውጊያ ቴክኒክ ት/ቤት ይሆናል፡፡
  5. የውጊያ ቴከኒክ ት/ቤት እንደ አስፈላጊነቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  6. ለማብራሪያና ጨረታ ሰነድ ማስገቢያ፡-

ሀ. ተጫራቾች ለሚኖራቸው ጥያቄ፡-

የውጊያ ቴክኒክ ት/ቤት ግዥ ዴስክ

ስልክ ቁጥር፡- 033-5-40-0612/ 09-24-84-62-69

ፋክስ ቁጥር፡- 033-5-40-06-66

ለ. ጨረታ ሰነድ ማስገቢያ፡-

የውጊያ ቴክኒክ ት/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ

ስልክ ቁጥር፡- 033-5-40-06-12

ቢሮ ቁጥር፡- 39

ሐ. ሰነዱ ወጪ የሚሆንበት አድራሻ፡-

የውጊያ ቴክኒክ ት/ቤት ፋይናንስ ዴስክ

ስልክ ቁጥር፡- 033-5-40-06-17

ቢሮ ቁጥር፡- 07

መ. ጨረታው የሚከፈትበት አድራሻ፡- 6/ለ/ ይመልከቱ፡፡

 

በኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የውጊያ ቴክኒክ ት/ቤት

 

Save Tender