Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጎንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
  • Address ጎንደር ከተማ : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0911-66 49 88
  • Website
  • Deadline14 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-14 00:00:00
  • Categories Transportation Service And Cargo

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጐንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለአዘዞ-ጎንደር መንገድ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚሆን ብዛቱ 1,760 በርሜል 80/100 አስፋልት (ሬንጅ) ከአዲስ አበባ (ቃሊቲ) ወደ ጐንደር (ማክሰኝት) እና 4,200 ኩንታል ሲሚንቶ ከለሚ-ጎንደር ከተማ ድረስ በጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል።

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጎንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪክት


 

ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዢ ጨረታ ቁጥር

GN-033/2017

 

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጐንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለአዘዞ-ጎንደር መንገድ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚሆን ብዛቱ 1,760 በርሜል 80/100 አስፋልት (ሬንጅ) ከአዲስ አበባ (ቃሊቲ) ወደ ጐንደር (ማክሰኝት) እና 4,200 ኩንታል ሲሚንቶ ከለሚ-ጎንደር ከተማ ድረስ በጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ እና የንግድ ምዝገባ ፈቃዳቸው በቂ የጭነት ትራንስፖርት አቅም ያላቸው ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ (የመልካም ሥራ አፈፃፀም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ) ድርጅቶች ለዚህ ጨረታ ሲባል የተዘጋጀውን ሰነድ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር እቃ ግዥ ቡድን 1 እና ቡድን 2 ቢሮ ወይንም ጎንደር ከሚገኘው የዲስትሪክቱ ጽ/ቤት በነፃ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን ከ15ኛው ቀን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር እቃ ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡

ከዚህ በፊት ከመ/ቤታችን ጋር የጭነት ማጓጓዝ ውል ወስደው የውል ግዴታቸውን በወቅቱ ያልፈፀሙ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የማይችሉ መሆኑን እያሳሰብን መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0911-664988/0925-356890

በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

 

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጎንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪክት

 

Save Tender