Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian sugar industry group Omo kuraz 1 & 3 Sugar Factory (በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ ጽ/ቤት)
  • Address አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ቢሮ ተዘንአ አጠቃላይ ሆስፒታል በሚያስገባው አስፓልት ከጦር ሃይሎች ወደ ዘነበ ወርቅ በሚወስደው መንገድ በተለምዶ 3 ቁጥር ማዞሪያ / ቶታል ገባ ብሎ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንፃ ላይ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 251910120628
  • Website
  • Deadline17 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-17 00:00:00
  • Categories Vehicle , Agricultural Materials , Machinery And Vehicles , Machinery Spare Parts

በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ጽ/ቤት ለተለያዩ ትራክተሮች፣ ጀነሬተር እና ለአገዳ ማጓጓዣ ጋሪዎች (YTO Tractor Model 1804፣ URSUS Tractor Model 14014A: YTO Tractor Model 1304/1004 Generator Spare part (400KVA): KAT Cane Carts: URSUS Cane Carts spare Part እና Beiben Truck Trailer/Cart) ጥገና አገልግሎት የሚውሉ መለዋወጫዎች በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian sugar industry group Omo kuraz 1 & 3 Sugar Factory (በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ ጽ/ቤት)


 

ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- LP/OT/016/0KSF1&3/2017

 

በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ጽ/ቤት ለተለያዩ ትራክተሮች፣ ጀነሬተር እና ለአገዳ ማጓጓዣ ጋሪዎች (YTO Tractor Model 1804፣ URSUS Tractor Model 14014A: YTO Tractor Model 1304/1004 Generator Spare part (400KVA): KAT Cane Carts: URSUS Cane Carts spare Part እና Beiben Truck Trailer/Cart) ጥገና አገልግሎት የሚውሉ መለዋወጫዎች በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

  1. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሰነድ ጋር ህጋዊ የታደሰ አዲስ የንግድ ፈቃድ፤ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፤ በተጨማሪም ተጫራቾች የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከሚመለከተው አድራሻ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00፤ ከሰዓት ከ7፡00-10፡30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00 ሰዓት) ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ ገዝተው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

ኦሞ ኩራዝ 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ

ገዥ ቡድን (ማስተባበር ቢሮ)

አድራሻ፡- ኮልፌ ቀራኒዮ፣ ከጦር ሃይሎች ወደ ዘነበ ወርቅ በሚወስደው መንገድ

በተለምዶ 3 ቁጥር ማዞሪያ/ ቶታል ገባ ብሎ

የፌድራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንፃ ላይ ቢሮ ቁጥር 1371/125

የስልክ ቁጥር (አድራሻ)፡-+251-9-63-44-28-82/ +251-9-10-12-06-28/

+251-9-16-17-08-34

አዲስ አበባ

  1. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ሎት የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንከ ጋራንቲ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በ10/11/2017 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን በ10/11/2017 ዓ.ም በ4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
  3. የጨረታው ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው፡፡
  4. የጨረታው ማስረከቢያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ ለ 90 ቀናት ነው፡፡

ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩኘ የኦሞ ኩራዝ 1 አና 3 ስኳር ፋብሪካ ጽ/ቤት

 

Save Tender