በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን በስሩ የሚገኙ ተሽከርካሪዎች የጥገና እና እድሳት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር መሰፋ/ብ/ግ/ጨ/011/2017
በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን በስሩ የሚገኙ ተሽከርካሪዎች የጥገና እና እድሳት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- በናፍጣ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች
- በቤንዚን የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች
በዚህም መሠረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው የምትሳተፉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ /VAT Registration Certificate/፤ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተመዘገቡ እና የቲን ሰርተፍኬት የብቃት ሰርተፍኬት Tax clearance certificate የመንግሰት የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መሰፋ ግዥ ቡድን ክፍል ቢሮ ቁጥር 015 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ማለትም 250,000 /ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ በተመሰከረለት/ሲ.ፒ.ኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት ባንክ ጋራንቲ ብቻ በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ስም ከጨረታው ኦርጅናል ቴክኒካል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ሰነዶቻቸውን ኦርጅናል እና አንድ አንድ ኮፒ ለየብቻ ተለይቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቢሮ ቁጥር 015 በመምጣት መሥሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። እንዲሁም ተያያዥ ዶክመንቶች ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ከጠዋቱ 8፡30 መ.ሰ.ፋ ግዥ ቡድን ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸው በጽሁፍ የሚገለጽላቸው እና የውል ስምምነት የሚፈፅሙ ይሆናል።
- በጨረታ ያላሸነፉ ድርጅቶች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
- ፋውንዴሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 011 557 2734
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው ላንድ ማርክ ሆስፒታል አጠገብ
የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን
