Tender Detail


በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሐራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

የሀራጅ ጨረታ ቁጥር 047/2017

 

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሐራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት፡-

በሀራጅ ጨረታ ቁጥር 047/17 በ25/10/2017 የተለያዩ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ጫማዎች፣ ስፔርፓርቶች፣ የሞባይል ቀፎዎች፣ ጎማዎች፣ ኮስሞቲክሶች እና የንጽህና መጠበቂያዎች፣ መነጽሮች፣ የእጅ ሰዓቶች፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የቤት እና የቢሮ ዕቃዎች፣ የተለያዩ መገጣጠሚያ እና ቆርቆሮ ዴክራ እና የተለያዩ ዕቃዎች ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ በመሽጥ ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ በመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች

  1. በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ እና መለያ ቁጥሩን ማቅረብ የሚችል መሆኑን ይጠበቅበታል፡፡
  2. ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች የሚገኙት በድሬዳዋ መድአነኖ ጊቢ ውስጥ በሚገኘው የውርስ ዕቃ መጋዘን ውስጥ ነው፡፡
  3. በሀራጅ ጨረታው ላይ በመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተጠቀሰው ቀን መሰረት ድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ገቢ አሰባሰብ እና ሦስትና አያያዝ ቡድን ገንዘብ ያዥ ቢሮ በመቅረብ ብር 100 በመክፈል ሪሲት በመውሰድ ዘወትር በስራ ሰአት ከሰኞ ስስከ አርብ ከጠዋቱ 1፡30 እስከ ቀኑ 12 ሰአት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2 ሰአት እስከ ቀኑ 6 ሰአት ንብረቱ በሚገኝበት መጋዘን በመቅረብ ማየት ይቻላል፡፡ ነገር ግን ለቃዎቹን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር ቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  4. ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ በድሬዳዋ ሙድአነኖ ጊቢ ነው፡፡
  5. በሀራጅ ጨረታ በሽያጭ የቀረቡት እቃዎች በኮድ የተከፋፈለ ሲሆን ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት፡፡
  6. ተጫራች በሀራጅ ጨረታ በመጫረት ዕቃዎች በመግዛት በሚያቀርበው ዋጋ 5% ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) በባንክ (ንግድ ባንክ) የተረጋገጠ በድሬዳዋ ጉምሩከ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. በሀራጅ ጨረታ ለወጡት ለያንዳንዱ ኮዶች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) የዕቃውን ዋጋ 5% ብር በባንክ (ንግድ ባንክ) የተረጋገጠ በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል።
  8. የሀራጅ ጨረታ በሚካሄደው በማስታወቂያ መሰረት በእለቱ ጠዋት በ2፡00 ሰዓት ምዝገባ ጀምረን እንደተጠናቀቀ በ4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ጨረታው ይጀምራል።
  9. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች እጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፍለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒኦ በሶስት የስራ ቀናቶች ውስጥ ተመሳሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  10. አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደረበትን እቃዎች አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል፡፡
  11. ከላይ በተራ ቁጥር 10 ላይ በተገለጸው ቀናቶች ውስጥ ከፍያውን ፈጽሞ ዕቃውን ያልተረከበ ተጫራች በጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ለባለስልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል፡፡
  12. የጉምሩክ ኮምሽን ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 15 46 09 70 (09 12 88 57 46) መደወል ይቻላል፡፡

 

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender