በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በት/ትና ስልጠና ዋና መምሪያ የመለስተኛ ስታፍ ኮሌጅ ለ2018 ዓ/ም ባለው በጀት ለመ/ቤታችን ሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጡ 62 ሰው የሚይዝ ደረጃ 1 አውቶብስ፤ 16 ሰው የሚይዝ ደረጃ ሀይሩፍ ሚኒባሶችን እና በአካባቢው ካሉ የሆቴል አገልግሎት ለማግኘት ሆቴሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር የውል ስምምነት በመፈጸም አገልግሎት ለማግኘት ይፈልጋል፡፡
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የመለስተኛ ስታፍ ኮሌጅ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር መ/ስ/ኮ/ግ/ጨ/001/18
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በት/ትና ስልጠና ዋና መምሪያ የመለስተኛ ስታፍ ኮሌጅ ለ2018 ዓ/ም ባለው በጀት ለመ/ቤታችን ሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጡ 62 ሰው የሚይዝ ደረጃ 1 አውቶብስ፤ 16 ሰው የሚይዝ ደረጃ ሀይሩፍ ሚኒባሶችን እና በአካባቢው ካሉ የሆቴል አገልግሎት ለማግኘት ሆቴሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር የውል ስምምነት በመፈጸም አገልግሎት ለማግኘት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መመሪያዎች
- ተጫራቾች በሁሉም በዘርፎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ መመዝገባቸውን ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ ለመኪና አገልግሎት ማህበራትን ጨምሮ ሲሆን ማህበሩ በትራ/ሚኒስቴር የድጋፍ ደብዳቤ ማስረጃ ዓመታዊ የመኪና የተሽከርካሪ ቦሎ ከኢንሹራንስ ድርጅት ኢንሹራንስ የገቡበትን ዋስትና እና የሶስተኛ ወገን እንዲሁም የግብር ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ባወጣው የመንግስት ግዥ አዋጅ መሠረት ብቁ ለሆኑ ተጫራቾች ነው።
- ፍላጎት ያላቸው ብቁ ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ሊያገኙ የሚችሉት በመለስተኛ ስታፍ ኮሌጅ ሲሆን የጨረታው ሰነዱ የሚመረመርበት ከዚህ በታች በተራ ቁ/7/ሀ/ በተገለጸው አድራሻ ነው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የተሟላና በአማርኛ የተዘጋጁ ሰነዶችን በተራ ቁጥር 7/ለ/ በተገለጸው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ፡፡ የጨረታው ሰነድ የሚላከው በተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ሲሆን ሰነዱ ቢጠፋ ወይም ቢዘገይ ኃላፊነቱን የማንቀበል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች ተ.ቁጥር 7/ሐ/ በተገለጸው አድራሻ እስከ 15/11/2017 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ድረስ አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሰነዱ ሽያጭ በተከታታይ ቀናት ይከናወናል፡፡ በተጨማሪም ተጫራቾች ለጨረታ ሰነዱ ማስከበሪያ ለሁሉም ዘርፎች በኢትዮጵያ ከታወቀ ባንክ በሲ.ፒ.ኦ ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር 7/መ/ በተገለጸው አድራሻ በ15/11/2017 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ 8፡30 ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያና ሰነድ ማስገቢያ፡-
- ተጫራቾች ለሚኖራቸው ጥያቄ
ሀ/ ዘወትር በስራ ሰዓት በአፋር ብ/ክ/መንግስት አዋሽ ሰባት ኪሎ
በመለስተኛ ስታፍ ኮሌጅ ግዥ ዴስክ ቢሮ
- ስልክ ቁጥር፡- 033 540-06-19 / 09 22 83 96 24
- ፋክስ ቁጥር 033 540-04-30
ለ/ የሰነዱ ሽያጭ የሚከናወንበት አድራሻ ተ.ቁጥር 6/ሀ/ላይ ይመልከቱ።
ሐ/ ጨረታው የሚላክበት አድራሻ፡-ተ/ ቁጥር6/ሀ/ ላይ ይመልከቱ።
ጨረታው የሚከፈትበት አድራሻ፡-ተ/ቁጥር 6/ሀ/ ይመልከቱ
- አገልግሎት የሚሰጠው በመለስተኛ ስታፍ ኮሌጅ በአዋሽ ሰባት ኪሎ ነው።
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የመለስተኛ ስታፍ ኮሌጅ
