Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ይርጋለም ማረሚያ ተቋም
  • Address ይርጋለም : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046 225 24 03
  • Website
  • Deadline10 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-10 00:00:00
  • Categories Food And Beverage , Firewood , Merchandise

የሲዳማ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ይርጋለም ማረሚያ ተቋም ለህግ ታራሚዎች የተለያዩ የምግብ ማጣፈጫዎች እና የምግብ ማብሰያ የማገዶ እንጨት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።  

የሲዳማ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ይርጋለም ማረሚያ ተቋም


 

ለህግ ታራሚዎች ለምግብ ማጣፈጫዎች እና ለምግብ ማብሰያ የሚሆን ማገዶ እንጨት ጨረታ ማስታወቂያ የግዥ ጨረታ ቁጥር 05/2017

 

የሲዳማ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ይርጋለም ማረሚያ ተቋም ከሀምሌ 1/2017 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30/2018 ዓ.ም ድረስ ለ6 /ስድስት/ ተከታታይ ወራት የሚቆይ ለህግ ታራሚዎች የተለያዩ የምግብ ማጣፈጫዎች እና የምግብ ማብሰያ የማገዶ እንጨት ግዥ ለመፈጸም ከዚህ በታች የተመለከቱትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።  

 

ተ.ቁ

የዕቃው ዓይነት

መለኪያ

ተ.ቁ

የዕቃው ዓይነት

መለኪያ

1

ዛላ በርበሬ ያልተፈጨ/

በኩንታል

9

ሠፌዱ

በቁጥር

2

የምግብ ጨው

     »    »

10

ካሜራ 500 ግራም

በፖኬት

3

ጎመን ዘር

     »    »

11

እርድ

በኩንታል

4

ቀይ ሽንኩርት

     »    »

12

ቃሪያ

በኪ/ግራም

5

ነጭ ሽንኩርት

     »    »

13

በቀርከሃ የተሰራ አክንባሎ

በቁጥር

6

ዝንጁብል

     »    »

14

በፍልጥ የተዘጋጀ የማገዶ እንጨት

በሜ/ኩብ

7

ሻይ ቅጠል ባለ 80 ግራም

     »    »

15

በግንድላ የተዘጋጀ የማገዶ እንጨት

በሜ/ኩብ

8

የእንጀራ ምጣድ

     »    »

16

ምስር

በኩንታል

 

ከላይ በዝርዝር የቀረቡትን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት ጨረታው የሚካሄደው በአማረኛ ቋንቋ ሲሆን በሚወዳደሩበት የንግድ ሥራ ዘርፍ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይነት ማስረጃ ያለው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፤ በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበ፤ በጨረታ መወዳደር የሚያስችል ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉና በአቅራቢነት ዝርዝር ለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ የያዘ በባንክ የተረጋገጠ  ሲፒአ ማቅረብ የሚችሉና በጨረታ የተጠቀሱ መስፈርቶችን የሚያማሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /ለአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የማይመለስ የኢትዮጵያ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከይርጋለም ማረሚያ ተቋም ገዝተው ከሞሉ በኋላ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ 15ኛው ቀን 8፡30 ሰዓት ድረስ ወደ ጨረታ ሳጥን አስገብተው በዚሁ ቀን 8፡35 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ በዕለቱ ከቀኑ 8፡40 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይርጋለም ማረሚያ ተቋም ላይ ይከፈታል። የጨረታው ሰነድ ለውድድር አቅርበው ከግል ምክንያታቸው የተነሳ በእለቱ የማይገኙ ተጫራቾች ካሉ ጨረታው ተከፍቶ ውጤቱ ይገለጽላቸዋል፡፡ አንድ ተጫራች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችልም። በጨረታው ሰነድ የተመለከቱትን ዓይነቶች ከላይ በሰንጠረዥ ውስጥ በተገለጸው መሠረት ይሆናል፡፡ የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸ ጊዜ ጀምሮ የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ አቅርበው ውል መፈጸም አለባቸው። አሸናፊዎች አሸናፊነታቸው እንደተገለጸ ውል የማይፈጽሙ ከሆነ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ አይመለስም፤ ይወረሳል። የጨረታው ዝርዝር በጨረታው የአፈጻጸም መመሪያ ላይ የተገለጸ ስለሆነ በይበልጥ ተቀባይነት ያለው የጨረታ ሰነድ በመሆኑ አንድ በአንድ ማንበብ ይኖርባቸዋል። ጨረታ አውጭው መ/ቤት የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ መረጃ 046 225 24 03 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ

 

ይርጋለም ማረሚያ ተቋም

ይርጋለም

 

Save Tender