የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዝ ለዩኒቨርሲቲ ለድለባ ፕሮጀክት የሚሆን የቁም ከብት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዝ ኃላ/የተ/የግል ማህበር
በድጋሚ የወጣ ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዝ ለዩኒቨርሲቲ ለድለባ ፕሮጀክት የሚሆን የቁም ከብት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ ጨረታውን ለመወዳደር የሚፈልጉ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች ግለሰቦች በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
- በዘርፉ የተመዘገበ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድና የንግድ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የታክስ መለያ ቁጥር (TIN-No) ያላቸው።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚኖሩት 15 የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ/ በመክፈል ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ፣ ፖሊሲ ልማትና ጥናት ተቋም ሕንፃ ላይ ከሚገኘው ከኢንተርፕራይዙ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቀርበው የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) በጥሬ ገንዘብ፣ በባንክ በተረጋገጠ ጋራንቲ ወይም /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚትወዳደሩበትን የተሟላ የቴክኒካልና የፋይናንሻል ሠነድ ኦሪጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ተከታታይ ቀናት እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 11፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ሆኖም ግን ጨረታ የሚከፈበት ቀን የሳምንቱ እረፍት ቀን እና የህዝብ በዓላት ላይ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው ቀናት የሚከፈት ይሆናል።
- ጨረታ በሚከፈትበት እለት የቴክኒካልና ዶክመንት ብቻ ተከፍቶ ይነበባል።
- ጨረታው የቴክኒክ ግምገማ ውጤት እንደተጠናቀቀ የሚገለጽ ሲሆን በቴከኒክ ግምገማው ያላለፈ ተወዳዳሪ ለፋይናንሻል ውድድር አይቀርብም።
- የጨረታ ውድድሩ ሂደት እንደተጠናቀቀ የግዥ ውጤቱ በኢንተርፕራይዙ በኩል ለተወዳዳሪዎች ባስመዘገቡት አድራሻ አማካይነት ይገለጽላቸዋል።
- ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዝ ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር ዋና ጽ/ቤት፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ በፖሊሲ ልማትና ጥናት ተቋም ሕንፃ ወይም ተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በሚገኝበት ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ፣ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ፣
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር /0462122858/0924388128 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዝ ኃላ/የተ/የግል ማህበር
