በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/ መንግስት የካፋ ዞን የገ/ፃዲቅ ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታል ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የኦክስጅን ማምረቻ ማሽን ጥገናና መለዋወጫ በማቅረብ ሰርቪስ ማድረግ አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማስራት ይፈልጋል።
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መስተዳድር የካፋ ዞን የገ/ፃ/ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/ መንግስት የካፋ ዞን የገ/ፃዲቅ ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታል ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የኦክስጅን ማምረቻ ማሽን ጥገናና መለዋወጫ በማቅረብ ሰርቪስ ማድረግ አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማስራት ይፈልጋል።
- በዚሁ መሰረት ተወዳዳሪዎች የሚጠበቅባቸው ቅድመ ሁኔታዎች፡-
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ እና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው እንዲሁም ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋብ የሆኑ።
- በመንግስት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- በኦክስጅን ማምረቻ ሥራ ጥገናና ሰርቪስ በማድረግ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ቦንጋ ገ/ፃ/ሻዎ/አ/ ሆስፒታል 3ኛ ፎቅ ግዥ ንብረት አ/ር ቢሮ ቁ.22 በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር ለእያንዳንዱ ጨረታ 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ። ለእያንዳንዱ ጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ሲፕኦ በባንክ የተመሰከረ ማቅረብና ማስያዝ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋጋ በመሙላት ቦንጋ ገ/ፃ ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታል 3ኛ ፎቅ ግዥና ንብረት አ/ር 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ.22 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ላይ ፖስታዎችን ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ቦንጋ ገ/ፃሻ/አ/ ሆስፒታል 3ኛ ፎቅ ግዥና ንብረት አ/ር ቢሮ ቁ.22 ተጫራቾች /ሕጋዊ ወኪሎች/ በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራች ያሸነፈበትን የኦክስጅን ማምረቻ ሰርቭስ እስከ ገ/ፃ/ሻ/አ/ሆስፒታል ቅጥር ጊቢ በመገኘት ውል በመግባት ሰርቪስ ማድረግ የሚችል።
- ተጫራቾች ተማልቶ አለመገኘት ሂደቱን አያስተጓጉልም።
- አሸናፊ ድርጅት ማሸነፉ ሲረጋገጥ ያሸነፈበትን የጠቅላላ ዋጋ 10% ውል ማስከበሪያ ለማስያዝ በሆ/ሉ ስም በዝግ አካውንት ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ እና ማሸነፉ ከተረጋገጠበት ሰባት የሥራ ቀናት ቀርቦ የውል ስምምነት ለመፈፀም ፈቃደኛ የሆነ።
- ጨረታው የሚከፈተው ቦንጋ ገ/ፃ/ሻ/አጠ/ሆስፒታል 3ኛ ፎቅ ግዥና ንብረት አ/ር ቢሮ ቁ.22 ሲሆን ቅዳሜ እና እሑድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ የሚቀጥለው የሥራ ቀን ላይ ይሆናል።
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 047 331 0316/047 331 2361 ያገኙናል።
በካፋ ዞን የገ/ፃዲቅ ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታል
