Tender Detail

Tender Details

  • Company በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወንጀል ጉዳይ ችሎት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 275 1911
  • Website
  • Deadline23 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-24 00:00:00
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

የሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወንጀል ጉዳይ ችሎት በአፈፃፀም ከሳሽ የኦሮሚያ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ቢሮ እና በአፈፃፀም ተከሳሽ አስቻለው ሸዋ ኔሪ ጣልቃ ገብ ነፃነት ረጋሳ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክርክርን በተመለከተ የዚህ አፈፃፀም ተከሳሽ ንብረት የሆነው ባለ ሦስት ወለል (ጂ+3) ህንጻ እና በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ውስጥ የሚገኝ መኖሪያ ቤት በግልጽ ጨረታ ስለሚሸጥ በጨረታው ላይ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች እንድትሳተፉ ይጋብዛል።

በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወንጀል ጉዳይ ችሎት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአፈፃፀም ከሳሽ የኦሮሚያ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ቢሮ እና በአፈፃፀም ተከሳሽ አስቻለው ሸዋ ኔሪ ጣልቃ ገብ ነፃነት ረጋሳ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክርክርን በተመለከተ የዚህ አፈፃፀም ተከሳሽ ንብረት የሆነው ባለ ሦስት ወለል (ጂ+3) ህንጻ የካርታ ቁጥሩ 02/104/9623/5/23/29031/02 ተመዝግቦ በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ውስጥ በ94 (ዘጠና አራት) ካ.ሜ መሬት ላይ ተሠርቶ የሚገኝ መኖሪያ ቤት የብር 8,176,130.35 (ስምንት ሚሊየን አንድ መቶ ሰባ ስድስት ሺህ አንድ መቶ ሰላሳ ከ35/100) ዕዳ ስለሚፈለግበት የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 18,549,123.05 /አስራ ስምንት ሚሊየን አምስት መቶ አርባ ዘጠኝ ሺህ አንድ መቶ ሀያ ሶስት ከ05/100) ጀምሮ ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች በግልጽ ጨረታ ስለሚሸጥ ከቀን 16/10/2017 ዓ.ም ጀምሮ አስከ 16/11/2017 ዓ.ም ለአንድ ወር አየር ላይ ቆይቶ በቀን 17/11/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 - 5፡00 ስለሚዘጋ መግዛት የምትፈልጉ ሰዎች ከቀን 17/11/2017 ዓ.ም ጀምሮ ቤቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት መግዛት እንደምትችሉ የሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ያሳውቃል።

ማሳሰቢያ፡- በዚህ የጨረታ ውድድር ላይ መሣተፍ የሚፈልጉ ሰዎች የጨረታውን ማስያዣ የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4ኛ ሲፒኦ ይዘው መቅረብ አለባቸው፤ እንዲሁም የጨረታው አሸናፊ የሆነ ሰው በቀጠሮው ቀን ያሸነፈበትን ገንዘብ በሙሉ ከፍሎ የሚያጠናቅቅ ይሆናል።

 

በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወንጀል ጉዳይ ችሎት

 

Save Tender