በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የሚገኘው ወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ ከዚ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአምራች፤ ከጅምላ አቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል።
ወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህ/ስ/ማህበራት ዩኒየን ኃላ/የተ
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የሚገኘው ወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ ከዚ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአምራች፤ ከጅምላ አቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1፡- ልዩ ልዩ አግሮ ኬሚካሎች/ ፀረ-ነፍሳት፣ ፀረ-አረም፣ ፀረ-ፈንገስ/
ሎት 2፡- ልዩ ልዩ የእንሰሳት መድኃኒቶች እና መገልገያ መሳሪያዎች፣
ከላይ በሎት 1 /አንድ/ እና 2 /ሁለት/ የተዘረዘሩትን ምርቶች ከሀገር ውስጥ ገበያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አምራቾች እና የጅምላ አከፋፋዮች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ዩኒየኑ እየገለጸ በጨረታው ለመሳተፍ፡-
- ከላይ በሎት አንድ /1/ እና ሁለት /2/ በተዘረዘሩት የንግድ ዘርፎች ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት/
- የበጀት ዓመቱን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው /Tax clearance/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት /ቲን ነምበር/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የቫት ሰርተፊኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
- ለሽያጭ የሚያቀርቧቸውን ምርቶች ዝርዝር መግለጫ የያዘ ጨረታ ሰነድ ከዩኒየኑ መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለአንድ ሎት የማይመለስ ብር 250 /ሁለት መቶ ሃምሳ ብር/ በዩኒየኑ አካውንት ቁጥር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠባሴ ቅርንጫፍ 1000082689967 በመክፈል በደ/ብርሃን ከተማ በጠባሴ አካባቢ ከመልዕክት አካዳሚ ጐን ከመኪና ማሰልጠኛው ፊት ለፊት በሚገኘው የወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማኅበራት ዩኒየን ኃላ.የተ ጽ/ቤት ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ከጠቅላላ ዋጋ 2% /ሲፒኦ/ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /ቢድ ቦንድ በሁለት ፈራሚ የተረጋገጠ በደ/ብረሃን እና አዲስ አበባ ባሉ ባንኮች በዩኒየኑ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ዶክመንት ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በሁለት ፖስታዎች ተለያይቶ በአንድ ፖስታ ታሽጎ በደ/ብርሃን ከተማ በጠባሴ አካባቢ ከመልዕክት አካዳሚ ጐን ከመኪና ማሰልጠኛው ፊት ለፊት በሚገኘው የወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃላ/የተ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጭምር እስከ 10ኛው ቀን /የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይቻላል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ብርሃን ከተማ በጠባሴ አካባቢ ከመልዕክት አካዳሚ ጐን ከመኪና ማሰልጠኛው ፊት ለፊት በሚገኘው የወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃላ/የተ/ ጽ/ቤት ጨረታው በጋዜጣ በወጣበት በ10ኛው ቀን /የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በደ/ብርሃን ከተማ በጠባሴ አካባቢ ከመልዕክት አካዳሚ ጐን ከመኪና ማሰልጠኛው ፊት ለፊት በሚገኘው የወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃላ/የተ/ጽ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር 011 681 4115 በመደወል ማግኘት ይቻላል።
በአብክመ በሰ/ሸዋ ዞን መስተዳደር ወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ኅ/ስ/ማህበራት ዩኒየን ኃላ/የተ/
ደ/ብርሃን
