ድርጅታችን ላሜ ዴያሪ ኃ.የተ.የግል ማህበር ዝርዝራቸው እና መለያ ዝርዝራቸው በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁትን ቋሚ ንብረት፤ ግብዓት እና አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ላሜ ዴያሪ ኃ.የተ.የግል ማህበር
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ላሜ ዴያሪ ኃ.የተ.የግል ማህበር ዝርዝራቸው እና መለያ ዝርዝራቸው በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁትን ቋሚ ንብረት፤ ግብዓት እና አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
1 |
ጀነሬተር 20 KVA |
|
2 |
ስኳር (white refined sugar) |
|
3 |
ጨው |
|
4 |
Caustic Soda |
|
5 |
Air ventilation system |
ስለዚህ፡-
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከመገናኛ ወደ ላምበረት መናኸሪያ በሚወስደው መንገድ ቶታል የነዳጅ ማደያን 50 ሜትር እንዳለፉ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የግዥ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 208 ድረስ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ7 የስራ ቀናት ውስጥ መግዛት ይቻላል።
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የሚያረጋግጥ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ከሚወዳደሩበት የዋጋ ማቅረቢያ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበትን የዕቃ ዓይነት ጠቅላላ ዋጋ 2% በላሜ ዴያሪ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ስም የተዘጋጀ የክፍያ ማዘዣ ከጨረታ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሠነዱ ላይ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ በመሙላት ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 7ተኛው ቀን ወይም 7ተኛው ቀን ዝግ ከሆነ በማግስቱ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ብቻ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ገቢ በማድረግ በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ። ጨረታው በተዘጋበት ዕለት ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መገናኛ ዋናው መስሪያ ቤት ይከፈታል።
- የጨረታ አሸናፊ የሆነ አቅራቢዎች ያሸነፉበትን ቋሚ ንብረት በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቀው ማስረከብ ይኖርባቸዋል። ይህ ካልሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት 2% ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል።
- አሸናፊ ድርጅቶች ለውል ማስከበሪያ ዋስትና 10% በላሜ ዴያሪ ኃ.የተ.የግል ማህበር ስም የተዘጋጀ የክፍያ ማዘዣ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማቅረብ ለዚሁ የተዘጋጀውን ውል መፈረም ይጠበቅባቸዋል።
- ድርጀቱ የተሻለ መንገድ ካገኛ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡- +251 116 73 36 35/ +251 116 47 97 89 / +251 116 46 00 53
ላሜ ዴያሪ ኃ.የተ.የግል ማህበር
