በኢትዮጰያ ጉምሩክ ኮሚሽን ባ/ዳር ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ለአንድ አመት የሚቆይ የዕቃ ጭነት እና የሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር፡-06/2017
በኢትዮጰያ ጉምሩክ ኮሚሽን ባ/ዳር ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ለአንድ አመት የሚቆይ የዕቃ ጭነት እና የሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች(አቅራቢዎች) ከዚህ በታች የተጠየቁትን መስፈርቶችና ግዴታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል። ተጫራች ከጨረታው መልስ ጋር የሚከተሉትን ተጨማሪ ሰነዶች ያቀርባል
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የቲን ሰርተፍኬት ያላቸውና ለጭነት አገልግሎት የባለቤትነት ማስረጃ ወይም ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ (ክሊራንስ) ማቅረብ የሚችሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ተሸከርካሪ መስመር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ለሎት፡- 2 የሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ 50,000.00/ሃምሳ ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይንም በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር በአፄ ቴወድሮስ ክ/ከተማ ወደ ዲያስፖራ በሚወስደው አስፓልት መንገድ ዘመን ኮንስትራክሽ ድርጅት ጎን በሚገኘው የጉምሩክ ኮሚሽን ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በጥንቃቄ በመሙላት በሚገባ በኤንቨሎፕ ፖስታ/ በማሽግ እና ተቋሙ ያዘጋጀው ሰነድ ዋጋ መሙያው ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በግልጽ በማስቀመጥ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ 3ኛ ፎቅ የግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 306 ጠዋት 4:30 ሰዓት ይከፈታል ነገር ግን 16 ኛው ቀን የህዝብ በዓል ወይም እሁድ ከሆነ በ17ኛው ቀን 4:00 ሰዓት ተዘግቶ 4:30 ሰዓት ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን የንግድ ማስረጃዎች ኦርጅናል ለብቻው አቅርበው ማሳየት ይኖርባቸዋል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 058 320 7051/058 320 6641/058 226 3346/
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ባ/ዳር ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
