በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን የእምድብር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለእምድብር ከተማ ሴከተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ በሎት የተከፈሉ ማለትም lote one የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች lote two ተሽከርካሪ (ሞተር ሳይክል) lote three ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን የእምድብር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
መለያ ቁጥር /004/2017
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን የእምድብር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለእምድብር ከተማ ሴከተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ በሎት የተከፈሉ ማለትም lote one የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች lote two ተሽከርካሪ (ሞተር ሳይክል) lote three ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም
- በንግድ ዘርፉ የተሰማራችሁ ተወዳዳሪዎች የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ ህጋዊ የታደሰ የስራ ፍቃድ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ፤ ቲን ነበር ፤ የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላችሁ፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታውን ሰነድ በማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ የእምድብር ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት በመክፈል ሰነዱን በእምድብር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዢ ክፍል በመምጣት መግዛት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ዶከመንታችሁ ላይ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ በማድረግ ከላይ በተራ ቁጥር 1 ላይ የተዘረዘሩ ማስረጃዎች 1 ኦርጅናል ሰነድና 2 ኮፒ በተለያዩ በታሸጉ ፖስታች በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባችሁ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 /አስር/ ቀናቶች አየር ላይ ይውላል እስከዛ ድረስ የጨረታ ዶክመታችሁን ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ ጨረታው የሚያበቃው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 /ስምንት ሰዓት/ ላይ የጨረታው ሳጥን ታሽጎ የዛኑ ቀን ከቀኑ 8፡30 /ስምንት ሰዓት ተኩል/ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ጨረታው ለመክፈት የሚያግድ ነገር የሌለ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- የሚከፈትበት ቀን በዓል /ቅዳሜና እሁድ/ ከሆነ ለሚቀጥለው የስራ ቀን ይተላለፋል፡፡
- ተወዳዳሪዎች በተወዳደሩበት በእያንዳንዱ ሎት ላይ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም ቢድ ቦንድ /bid bond/ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በእምድብር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም አሰርተው ከጨረታው ሰነድ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ
ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ /bid bond/ የምታቀርቡ ከሆነ 60 /ስልሳ/ ቀንና ከዚያ በላይ የሚቆይ መሆን አለበት ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ 0921542357/0926928268
በጉራጌ ዞን የእምድብር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
