Tender Detail

Tender Details

  • Company የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ
  • Address ቤኒሻንጉል ጉሙዝ : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0577750839
  • Website
  • Deadline09 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-09 00:00:00
  • Categories 3- Wheel Vehicle, Motorcycles And Bicycles , Camera

የቤ/ጉ/ክ/መ/ ጤና ቢሮ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ካሜራ እና 150 ሲሲ ሞተር ሳይክል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የቤ/ጉ/ክ/መ/ ጤና ቢሮ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ካሜራ እና 150 ሲሲ ሞተር ሳይክል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል። በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል።

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ፈቃዳቸውን ዋናውን ፎቶ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ የሚችሉ
  2. የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /Tin Number/
  4. የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  5. የንግድ ምዝገባ ያላቸው
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /CPO/ 20,000 ማስያዝ የሚችሉ
  7. የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ/ ብር በመክፈል ከቤ/ጉ/ክ/መ/ጤና ጥበቃ ቢሮ ቁጥር 13 በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ።
  8. የመወዳደሪያ ዋጋ መሞላት ያለበት በኢትዮጵያ ብር መሆን አለበት።
  9. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ተመስርቶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  10. ተጫራቾች አሸናፊ የሆነባቸውን ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ በጨረታ ሠነዱ ላይ በተያያዘው ስፔስፊኬሽን (specification) መሠረት ማቅረብ የሚችሉ።
  11. የጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት ዕቃውን በራሱ ወጪ ቤ/ጉ/ክ/መ/ጤና ጥበቃ ቢሮ ድረስ ማምጣት ይጠበቅበታል።
  12. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለ15 የስራ ቀናት የጨረታ ሠነድ በመግዛት በሰም በታሸገ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው ቀን ከሰዓት በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 8:30 ሰዓት ስለሚከፈት በቤ/ጉ/ክ/መ/ጤና ጥበቃ ቢሮ ቁጥር 13 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን እናስታውቃለን፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታው ሠነድ አይስተጓጐልም።
  13. የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀናት ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀናት ይሆናል።
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  15. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለግዎ በስልክ ቁጥር 0577750839 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ

 

Save Tender