Tender Detail

Tender Details


የሚኒስቴር መ/ቤቱ ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን የታክስ ዕዳ በታክስ ህጉ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ባለመክፈላቸው ምክንያት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 41 በተሠጠው ስልጣን መሠረት የግሪን ላንድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር 30,000 ካሬ ላይ ያረፈ ሪዞርት እስከነ ሙሉ ዕቃው፣ የሜጋ ቪሌጅ ሪልእስቴት ኃ/የተየግ/ማህበር የኮንስተራክሽን እቃዎች (እስካፎልዲንግ) ፣ ከኡኑምፕሬሳ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር የኮንስትራክሽን ተሽከርካሪ፣ የፎኒከስ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር (ዮፕላስቲክ ገመድ ማምረቻና የምርት ግብአት) ፣ የFKD ትሬዲንግ የተለያዩ የሬስቶራንት ዕቃዎች እና ከተለያዩ ድርጅቶች የተያዙ የተለያየ ሞዴል ያላቸው 20 ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

Ministry of Revenues (የገቢዎች ሚኒስቴር)


 

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገቢዎች ሚኒስቴር በታክስ ዕዳ የያዘውን 30000 ካሬ ላይ ያረፈ ሪዞርት፤ የተለያየ ሞዴል ያላቸው ተሽከርካሪዎችና ለሎች ንብረቶች ለመሸጥ የወጣ የግልጽ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁ-8/2017

 

የሚኒስቴር መ/ቤቱ ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን የታክስ ዕዳ በታክስ ህጉ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ባለመክፈላቸው ምክንያት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 41 በተሠጠው ስልጣን መሠረት የግሪን ላንድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር 30,000 ካሬ ላይ ያረፈ ሪዞርት እስከነ ሙሉ ዕቃው፣ የሜጋ ቪሌጅ ሪልእስቴት ኃ/የተየግ/ማህበር የኮንስተራክሽን እቃዎች (እስካፎልዲንግ)፣ ከኡኑምፕሬሳ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር የኮንስትራክሽን ተሽከርካሪ፣ የፎኒከስ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር (ዮፕላስቲክ ገመድ ማምረቻና የምርት ግብአት)፣ የFKD ትሬዲንግ የተለያዩ የሬስቶራንት ዕቃዎች እና ከተለያዩ ድርጅቶች የተያዙ የተለያየ ሞዴል ያላቸው 20 ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም:-

  1. በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ማንነቱን የሚገልጽ የነዋሪነት መታወቂያ (ፓስፖርት) ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለግልፅ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ የግልፅ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት ህንፃ "ለ" 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ከግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የማይመለስ ብር 100.00 (እንድ መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ህንፃ "ሀ" 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ከታክስ ዕዳ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ መውሰድ ይኖርበታል።
  3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ንብረቶች የሰጡትን ዋጋ 1/10ኛውን ብቻ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) በገቢዎች ሚኒስቴር ስም (Minstry of Revenue) በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት ሰነድ ገዝተው መጫረት ይችላሉ።

ተ/ቁ

የመ/ቤቱ ስም

ለጨረታ የቀረበው የንብረት ዓይነት

የንብረቶቹ መመልከቻ ቀን

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

 

1

 

ገቢዎች ሚኒስቴር

በአርባ ምንጭ ከተማ የሚገኝ 30000 ካ.ሜ ላይ ያረፈ ሪዞርት ከነሙሉ ዕቃው፤ እስካፎልዲንግ፤ የተለያየ ሞዴል ያላቸው ተሽከርካሪዎች እና የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች

ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት

ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 15 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው 16ኛ ቀን 3፡45 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል

 

  1. የጨረታ መክፈቻ ቦታ:- መገናኛ በሚገኘው በሚኒስቴር መ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
  2. የግልፅ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ 16ኛው ቀን የመ/ቤቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን የግልፅ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ ቀን ይሆናል።
  3. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር እንደ አስፈላጊነቱ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የግልፅ ጨረታ ኮሚቴው መረጃውን አጣርቶ እንደጨረሰ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  4. የተሽከርካሪ ጨረታ ለሚያሸንፉ ተጫራቾች ከስመ-ንብረት ዝውውር ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ወጪዎች (የቦሎና ሌሎች ተጓዳኝ ወጪዎች) ሻጭን አይመለከትም።
  5. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ መ/ቤቱ በሚሠጠው አድራሻ ገቢ በማድረግ ያሸነፋበትን ሀብት/ንብረት መረከብ ይኖርባቸዋል።
  6. ከላይ በተ/ቁ 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ በማድረግ ንብረታቸውን ያልተረከቡ ተጫራቾች የግልፅ ጨረታው ተሠርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በCPO ያስያዙት የዋስትና ገንዘብ ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ንብረቱ እንዳልተሸጠ ተቆጥሮ በቀጣይ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
  7. ሚኒስቴር መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ የግልፅ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011-617-84-90 ኮድ (2044) (2045) (2046) የውስጥ መስመር (EXT) 2044 ደውለው መጠየቅ ወይም የተቋሙን ዌብሳይት WWW.MOR.Gov.et መመልከት ይቻላል።

 

የገቢዎች ሚኒስቴር

 

Save Tender