የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከላይ የተጠቀሰውን ብዛታቸው 22 የሆኑ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ
ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች የሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር፡-AAU/NCB/pd/06/2017/25
- የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከላይ የተጠቀሰውን ብዛታቸው 22 የሆኑ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
- ተሸርካሪዎቹ የሚገኙበት አድራሻ 6 ኪሎ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትራንስፖርትና ተሸከርካሪ ጥገና ከፍል ሲሆን ለመግዛት ፍላጎትና ብቃት ያላቸው ተጫራቾች በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነድ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንድታቀርቡ ተጋብዛችኋል፡፡
- ጨረታው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያ ሥነ-ሥርዓት መሰረት ይፈፀማል።
- ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7 (ሀ) በተገለፀው አድራሻ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በዩኒቨርሲቲው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000087392067 ገቢ በማድረግና ደረሰኙን ይዘው በመቅረብ ስለተሽከርካሪዎቹ ሙሉ ዝርዝር የያዘውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7 (ለ) በተገለጸው አድራሻ እስከ ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም እሰከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው በተጫራቾች መመሪያ በተዘረዘረው መሰረት አያይዘዉ ያቀርባሉ፡፡ ዘግይተዉ የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቁጥር 7 (ሐ) በተጠቀሰው አድራሻ ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጠዋት 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7 (ለ) በተገለጸው አድራሻ ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ወይም በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነዱን በማስገባት በግዥ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ከጨረታ መክፈቻ ጊዜ በፊት ማቅረብ አለባቸው። ተጋባዥ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ለአንድ ተሸከርካሪ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በዩኒቨርሲቲው ስም አሰርተው አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ ከወጣ የተያዘው የጨረታ ማስከበሪያ የሚወረስ ይሆናል፡፡
ሀ/ ሰነዶቹ የሚሸጡበት አድራሻ አዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 312
ለ/ የጨረታው ሰነድ የሚገባበት አድራሻ አዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 200
ሐ/ ጨረታው የሚከፈትበት አድራሻ አዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 200
- የጨረታ አሸናፊው ድርጅት የውል ስምምነት ከተፈረመበት ቀን በኋላ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ ለየኒቨረሲቲው ሙሉ ክፍያ በመፈጸም ከከፈለበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እቃውን አለበት፡፡
- ዩኒቨርሲቲው በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታዉን የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 011-122-00 01/011-124-32-72 ፖ.ሣ.ቁ 1176
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ
