Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፔፕሲ ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የሐዋሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት አዲሱ የውርስ መጋዘን ቅጥር ግቢ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462125896
  • Website
  • Deadline04 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-04 00:00:00
  • Categories Cleaning & Janitorial

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ በጉምሩክ ኮሚሽን ሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት የተተዉና የተወረሱ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድኃኒቶች የማስወገጃ ቦታ አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ግልጽ ጨረታ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 0013/2017 አውጥቷል።

በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ በጉምሩክ ኮሚሽን ሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት የተተዉና የተወረሱ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድኃኒቶች የማስወገጃ ቦታ አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ግልጽ ጨረታ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 0013/2017 አውጥቷል።

  • ስለሆነም ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የሥራ ፈቃድ፤ የዘመኑን ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው ማስረጃ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት የሚያሳይ ማስረጃዎችን አደራጅተው ማቅረብ የሚችሉ።
  • ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/እና የተጫራቾች መመሪያ የማይመለስ ብር 200 በመክፈል ወደ ዲላ በሚወስደው ዋና አስፓልት ከጨርቃ ጨርቅ ፊት ለፊት ባለው ላቀች ህንፃ ቢሮ ቁጥር 101 ሀብት አስተዳደር ስራ ሂደት በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
  • ተጫራቾች ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ በሲፒኦ ወይም መመሪያው በሚፈቅደው መሰረት ማቅረብ የሚችሉ።
  • ተጫራቾች በግዢ ኤጀንሲ ድረ-ገፅ (supplier list) ላይ የተመዘገቡ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል/ካለ/፤
  • ተጫራቾች የመወዳደሪያ ቴክኒክና የፋይናንሽል ዋናውንና አንድ ኮፒ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸጉ ፖስታ ለብቻ ለብቻ በማድረግ ቢሮ ቁጥር 101 አንደኛ ፎቅ አስተዳደር ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
  • የጨረታው ሣጥኑ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወደ ዲላ በሚወስደው ዋና አስፓልት ከጨርቃ ጨርቅ ፊት ለፊት ባለው ላቀች ህንጻ ምድር ላይ በሚገኘው ሻይ ክበብ ውስጥ ይከፈታል።
  • ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ማሳሰቢያ ማብራሪያ ቢያስፈልጎ የስልክ ቁጥር፡- 046-2-12-65–02/ 046-2-12-56-90 ይጠቀሙ።

 

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጉምሩክ ኮሚሽን ጉምሩክ ሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender