Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል
  • Address አባ ሳሙአል ማረሚያ ማዕከል : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114-39-76-61
  • Website
  • Deadline27 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-27 00:00:00
  • Categories Food And Beverage , Firewood

የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ለህግ ታራሚዎች ምግብ አገልግሎት የሚውሉ ጥራጥሬዎች እንዲሁም አትክልትና ማጣፈጫዎች የማገዶ እንጨት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅቶች መግዛት ይፈልጋል።

በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- 1

 

የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ለህግ ታራሚዎች ምግብ አገልግሎት የሚውሉ ጥራጥሬዎች እንዲሁም አትክልትና ማጣፈጫዎች የማገዶ እንጨት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅቶች መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፡-

  1. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ፣ በሥራው መስክ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በዕቃ ግዢ አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዲሁም ቲን ቁጥር (Tin Number) ተመዝጋቢ የሆኑና ግብር ስለመክፈላቸው የተሟላ ማስረጃ ሊያቀርቡ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. ለህግ ታራሚዎች ለምግብ አገልግሎት የሚውሉ ጥራጥሬዎች እንዲሁም አትክልትና ማጣፈጫዎች የማገዶ እንጨት ለጨረታው የውል ማስከበሪያ ብር 60,000.00 (ስልሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች አንዱ በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም።
  4. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ (ፕሮፎርማቸው) በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በ4 ኮፒ አሽገው ማቅረብ አለባቸው።
  5. የጨረታ ቁጥር 1- ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነዳቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የግዥ ክንውን ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 ማስገባት ይችላሉ።
  6. ጨረታው በዚሁ ዕለት በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማረ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
  7. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል (አባ ሳሙኤል አዲሱ ማረሚያ ማዕከል) በሚገኘው ግ/ቤታችን ማስረከብ አለባቸው ማረ/ቤቱ የሚገዛቸው ዕቃዎች በጨረታ ሰነዱ ተዘርዝረው ቀርበዋል።
  8. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመስስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ቃሊቲ በሚገኘው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000007971188 ቃሊቲ ማረ/ቤት እደ/ጥ/ማዕከል በሚል ገንዘቡን ገቢ ካደረጉ በኋላ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  9. ተጫራቾች ጨረታ ሰነድ ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  10. ተጫራቾች ፕሮፎርማቸው ላይ ዋጋ ሲፅፉ ስርዝ ድልዝ የሌለበት መሆን ይገባዋል፤ ስርዝ ድልዝ ያለበት ዋጋ ተቀባይነት የለውም፤ በአሃዝና በፊደል መፃፍ ይጠበቅባቸዋል።
  11. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-4-39-76-61/ 011-4-39-49-16 ደውለው መጠየቅ ይችላሱ።

 

በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል

 

Save Tender