በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መጣቢዎች ተይዞው እና ተወርሰው የሚገኙ የሞተር ሳይክል እና የተሽከርካሪ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የሞባይል ቀፎዎች እና አክሰሰሪው (መገናኛ መሳሪያዎች) እንዲሁም ሌሎች ዕቃዎች በግልጽ እና በሃራጅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:- 35/2017
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መጣቢዎች ተይዞው እና ተወርሰው የሚገኙ የሞተር ሳይክል እና የተሽከርካሪ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የሞባይል ቀፎዎች እና አክሰሰሪው (መገናኛ መሳሪያዎች) እንዲሁም ሌሎች ዕቃዎች በግልጽ እና በሃራጅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ቅድመ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጡ ዕቃዎች ጋር ተዛማችነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና መለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የግልጽ ጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 – 12፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከ2፡00 - 6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በጽ/ቤታችን የእለት ገቢ ገንዘብ ሰብሳቢ ቢሮ በአካል በመገኘት ወይም በሞያሌ ጉምሩከ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተው ቀጥታ አካውንት ቁጥር 1000026238521) በስልክ ደውሎ ማሳወቅና ስሊፑን በቴሌግራም ቁጥር 09-12-64-12-94/ 09-48-08-48-48 በመላክ የጨረታ ሰነድ ባሉበት በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይቻላል፡፡
- በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና (CPO) እንዲሁም በሃራጅ ጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎችንም በተመለከተ የመግዣ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) በጉምሩክ ኮሚሽን በሞያሌ ቅርንጫፍ ስም በባንክ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚካሄደው በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ሲሆን ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ባሉበት ወይም ታዛቢ ፊት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር እሰከ 7ተኛው ቀን ድረስ ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች ናሙና በሞያሌ እና በሁሉም መ/ጣቢያ የሚገኙ መጋዝኖቻችን እየሄዱ ወይም በቃሊቲ ጉምሩክ ጌታስ መጋዘን (መጋዘን ቁጥር 8) መመልከት አለባቸው፡፡
- ጨረታው የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር በ8ኛው ቀን ሲሆን ጨረታው በ3፡45 (ሶስት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ) ተዝግቶ በ4፡00 (አራት ሰዓት) ላይ ይከፈታል፡፡
- ከላይ በተራ ቁጥር 6 በተገለጸው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር በ8ኛው ቀን የስራ ቀን ሳይሆን ቢቀር የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
- ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት ከተገለጸ በ 3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ 5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ በተራ ቁጥር 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት CPO ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09-12-64-12-94/ 09-48-08-48-48/09-07-25-41-94/046-4-44-15-64 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
