በመጣራት ላይ ያለው ጊዜ መሪ ማርኬቲንግ አ/ማ በይዞታው የሚገኘውን ኮድ3-47976 እ.አ 2003 ጃን ስሪት ቶዮታ አውቶሞቢል ፣ በጨረታ መሸጥ ይፈልጋል።
ተስፋዬ ተሰማ ሺበሺ የተመሠከረለት የሂሳብ አዋቂና የተፈቀደለት ኦዲተር (የሒሳብ አጣሪ)
በመጣራት ላይ ያለውን ጊዜ መሪ ማርኬቲንግ አ/ማ የአውቶሞቢል ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/ጊመጨ/2017
በመጣራት ላይ ያለው ጊዜ መሪ ማርኬቲንግ አ/ማ በይዞታው የሚገኘውን ኮድ3-47976 እ.አ 2003 ጃን ስሪት ቶዮታ አውቶሞቢል ፣ በጨረታ መሸጥ ይፈልጋል። ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት ተከታታይ አምስት የሥራ ቀኖች | ከሰኞ እስከ ዓርብ ዘወትር በሥራ ሠዓት ከታች በተጠቀሰው የአጣሪው አድራሻ ንብረቱን መመልከትና የጨረታ ሰነዱን ገዝተው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጀውን መኪና ዝርዝር ሁኔታ የያዘ የጨረታ ሰነድ ከታች በተቀሰው አድራሻ በአካል በመገኘት በብር 500 ሰነዱን በመግዛት መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሰኞ-አርብ ባሉት አምስት ተከታታይ የስራ ቀኖች ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት በአጣሪው አድራሻ በመገኘት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ይኽ የጨረታ መነሻና መዝጊያ ቀን በጨረታ ሰነዱ በማያሻማ ሁኔታ የሚገለፅ ይሆናል፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ እያንዳንዱ ተጫራች መኪናውን የሚገዙበትን ዋጋ 10% (አሥር በመቶ) ሲፒኦ በሚጣራው ድርጅት ስም አሰርቶ በታሸገ ፖስታ ከጨረታ ሠነዱ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ለጨረታው ለውድድር የሚቀርበው ተጫራች ቁጥር ከ3 ሰው ሲያንስ አጫራቾች ውድድሩን የመሰረዝ ፣ ድጋሚ ጨረታ የማውጣት ወይም ባለው እንዲወሰን የማድረግ መብታቸው የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው አምስተኛ የሥራ ቀን ከሰዓት በ8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ8፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ጨረታው በአጣሪው ይከፈታል።
- አሸናፊ ላልሆኑ ተጫራቾች ውጤቱ እንደታወቀ ያስያዙት ሲፒአ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘና አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው ጨረታውን በሙሉም ሆኖ በከፊል የመሠረዝ የጨረታ ጊዜ ገደቡን የማራዘም መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ከአፍሪካ ሕብረት ሚካኤል በስተግራ ካለው ሶስተኛ ቅያስ ከይሚ ሬስቱራንት በስተቀኝ ከሚገኘው ባለሰማያዊ ቀለም ቅብ ሕንጻ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 5 የቤት ቁጥር ብሎክ 3/403 2ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር፡- 0911429035/0115586377
ተስፋዬ ተሰማ ሺበሺ የተመሠከረለት የሂሳብ አዋቂና የተፈቀደለት ኦዲተር (ሒሳብ አጣሪ)
