የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዋና መ/ቤት፣ ፖስታ ቤት እና አቃቂ በሚገኘው መጋዘን ውስጥ መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል ያልቻሉ ያገልግሎት ጊዜያቸው ያበቃ ልዩ ልዩ ፕሪንተር ማሽኖች፤ ቴሌቪዥኖች፤ ፎቶ ኮፒ ማሽኖችን፣ ሲሊንደሮች፣ ሞኒተሮችና ሌሎች ቁሳቁሶችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
Ministry of Innovation and Technology (የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር)
ያገልግሎት ጊዜያቸው ያበቃ ልዩ ልዩ ፕሪንተር ማሽኖች፤ ቴሌቪዥኖች፤ ፎቶ ኮፒ ማሽኖችን፤ ሲሊንደሮች፤ ሞኒተሮችና ሌሎች ቁሳቁሶችን ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2017
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዋና መ/ቤት፣ ፖስታ ቤት እና አቃቂ በሚገኘው መጋዘን ውስጥ መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል ያልቻሉ ያገልግሎት ጊዜያቸው ያበቃ ልዩ ልዩ ፕሪንተር ማሽኖች፤ ቴሌቪዥኖች፤ ፎቶ ኮፒ ማሽኖችን፣ ሲሊንደሮች፣ ሞኒተሮችና ሌሎች ቁሳቁሶችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
- በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው እና ልዩ ልዩ ኤሌክትሮኒክሶች፣ ፕላስቲኮች፣ ጊዜያዊ ክምችት፣ የመነቃቀልና ድጋሚ የመጠቀም እንዲሁም ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃና መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ግቢ ውስጥ መሰረታዊ አገልግሎት ቢሮ በመምጣት የንብረቶችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ 200 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000263705916 ከፍለው ደረሰኝ በማምጣት መውሰድ ይችላሉ፣
- ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚወጣው ፕሮግራም መሰረት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ልዩ ልዩ ንብረቶችን ከላይ በተጠቀሰው መጋዘን በመሄድ መመልከት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የሚገዙትን ሙሉ ንብረቶች የጨረታ መነሻ ዋጋ 10 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ በሚ/ር መስሪያ ቤቱ ስም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚ/ር 3ኛ ፎቅ መሰረታዊ አገልግሎት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚ/ር 3ኛ ፎቅ ይከፈታል። ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል። እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ፈቃድ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፣
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፣
- የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው፡፡ የሚወዳደሩባቸውን ሙሉ ንብረቶች የመነሻ ዋጋ 10 በመቶ ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡
- የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣
- አገልግሎቱ ባወጣው ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፣
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0913-232728/0911907148/0973513788/0986-346652 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣
- መ/ቤቱ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የማያስችል ሁኔታ ከተፈጠረ በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
