በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉ፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ ተሽከርካሪዎችን በሀራጅና በግልጽ ጨረታ እንዲሁም የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
AA Kaliti Customs Office (አ.አ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት)
በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተያዙና የተወረሱ ተሽከርካሪ እና ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር፡- 47/2017
በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉ፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ ተሽከርካሪዎችን በሀራጅና በግልጽ ጨረታ እንዲሁም የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃ ተዘጋጅቶ ከሀሙስ ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በመሆኑም፡-
- በተሽከርካሪ ግልጽ ጨረታ ለመሣተፍ ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (CPO) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርበት ሲሆን ለተሽከርካሪ ሃራጅ ጨረታ ደግሞ ጨረታው ከመጀመሩ በፊት ይዞ ማስመዝገብ ይኖርበታል፡፡
- በግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (CPO) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርበት ሲሆን ለሃራጅ ጨረታ ደግሞ ከጨረታው አንድ ቀን በፊት ይዞ ማስመዝገብ ይኖርበታል።
- በጨረታው ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች የተሽከርካሪውን እና የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሀሙስ ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- በዕቃና በተሽከርካሪ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ወይም ተሽከርካሪዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በቅ/ፅ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የተሽከርካሪ ሀራጅ ጨረታ ለመሳተፍ ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪዎች ብር 100,000.00 እና የዕቃ ሐራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ለዕቃዎች ብር 100,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ ቼከ (CPO) በተ.ቁ 5 በተገለጸው አድራሻ ተጫራቹ ማስያዝ አለበት፡፡ ነገር ግን በዕቃ ሐራጅ በጨረታ ሰነድ ላይ በሚገለጹ የተወሰኑ ዕቃዎች ላይ የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) መጠን የሚወሰን መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ፡፡
|
ተ.ቁ |
የቅ/ጽ/ቤቱ ስም |
የጨረታው አይነት |
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት |
የእቃ ሀራጅ |
እስከ 16/10/2017 |
በ17/10/2017 ዓ.ም ከ4፡00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል። |
|
የእቃ ግልጽ |
እስከ 17/10/2017 |
በ18/10/2017 ዓ.ም በ3፡45 ሰዓት ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል። |
||
|
የተሽከርካሪ ግልጽ |
እስከ 17/10/2017 |
በ18/10/2017 ዓ.ም በ3፡45 ሰዓት ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል |
||
|
የተሽከርካሪ ሀራጅ ጨረታ |
እስከ 18/10/2017 |
በ19/10/2017 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል። |
- የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- ኢአ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡
- ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ በተ/ቁ 10 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ፡- 011-4-70-85-03
አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ ያለበት አዲሱ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ
አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
