በአፈጻጸም ክርክርን በተመለከተ በነቀምቴ ከተማ 04 ቀበሌ ውስጥ በፍርድ ባለእዳ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ስፋቱ 376 ካሬ ሜትር የሆነ የመኖሪያ ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ በወጣ የጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ስለሚሸጥ መግዛት የሚፈልግ ቀርባችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን የምስራቅ ወለጋ ዞን ፍርድ ቤት ያሳውቃል፡፡
የምስራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
የመጀመሪያ የጨረታ ማስታወቂያ
በፍርድ ባለሙበት አዱኛ ጎበና እና በፍርድ ባለእዳ ታከለ ሙሉ መካከል ባለው የአፈጻጸም ክርክርን በተመለከተ በነቀምቴ ከተማ 04 ቀበሌ ውስጥ በፍርድ ባለእዳ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ስፋቱ 376 ካሬ ሜትር የሆነ የካርታ ቁጥሩ 859/W/L/E/N/03 የመኖሪያ ቤት በምስራቅ ገመቹ አመኑ፣ በምእራብ ታደሰ ካሳሁን፣ በሰሜን መንገድ እና በደቡብ በቀበሌ ቤት መካከል የሚገኘውን የመኖሪያ ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ በወጣ የጨረታ ማስታወቂያ መነሻ ዋጋ በብር 2,011,308 (ሁለት ሚሊዮን አስራ አንድ ሺህ ሦስት መቶ ስምንት) በቀን 12/11/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00-6፡00 ድረስ አወዳድሮ ስለሚሸጥ መግዛት የሚፈልግ ከዚህ በላይ የተገለጸውን የመነሻ ዋጋ 1/4ኛውን በCPO በማስያዝ መኖሪያ ቤቱ በሚገኝበት ቦታ ቀርባችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን የምስራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያሳውቃል፡፡
የምስራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
