Tender Detail

Tender Details


ኩባንያችን ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ ተሽከርካሪዎችን ሞተር ሳይክል ፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች የቢሮ እቃዎች ፤ ጎማዎች ፣ የመኪና ባትሪዎች ፣ የተለያዩ የመኪና እቃዎች ፣ የቶነር ካርቲሬጆች ፣ የስልክ ቀፎዎች ፣ ሻተር መጋረጃና የመጋረጃ አክሰሰሪዎች እንዲሁም ምንጣፍ ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

BUNNA INSURANCE S.C (ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ)


 

ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ

 

የጨረታ ማስታወቂያ

Bunna Insurance Company (S.C)

 

ኩባንያችን ተሽከርካሪዎችን ሞተር ሳይክል ፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች የቢሮ እቃዎች ፤ ጎማዎች ፣ የመኪና ባትሪዎች ፣ የተለያዩ የመኪና እቃዎች ፣ የቶነር ካርቲሬጆች ፣ የስልክ ቀፎዎች ፣ ሻተር መጋረጃና የመጋረጃ አክሰሰሪዎች እንዲሁም ምንጣፍ ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ግዥውን ለመፈፀም የሚፈልጉ ተጫራቾች ሳርቤት ወይም አፍሪካ ህብረት ጀርባ በሚገኘው የኩባንያችን ዋና መ/ቤት ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) የጨረታ ሰነዱን በመግዛት ንብረቶቹን የሚገዙበት ዋጋ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መሠረት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ገቢ በማድረግ መጫረት ይችላሉ።

ማሳሰቢያ

  • ተጫራቾች ንብረቾችን እና ተሽከርካሪዎችን ቃሊቲ ሸዋ ዳቦ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ በሚገኘው የኩባንያው ሪከቨሪ ግቢ ውስጥ ከሰኔ 09 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ሰኔ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በመገኘት ማየት ይችላሉ።
  • ጨረታው ሰኔ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት የተገኙ ተጫራች ወይንም ተወካዮች በተገኙበት ይከፈታል።
  • ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
  • ተጫራቾች የሚጫረቱትን ንብረት ለሎት 01 የጨረታ ማስያዣ ብር 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) ፣ ለሎት ሁለት ብር 2,000 (ሁለት ሺህ ብር) ፣ ለሎት ሶስት ብር 4,000 (አራት ሺህ ብር) ፣ ለሎት አራት ብር 4,500 (አራት ሺህ አምስት መቶ ብር) ፣ ለሎት አምስት ብር 2,500 (ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር) ፣ ለሎት ስድስት ብር 1,500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) በቡና ኢንሹራንስ አ.ማ ወይም Bunna Insurance S.C ስም በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  • የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፋበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% (አስራ አምስት በመቶ) በተጨማሪነት ይከፍላሉ።
  • አሸናፊዎች የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባለው 10 የሥራ ቀን ውስጥ ክፍያ ፈጽመው ንብረቶቹን ካልተረከቡ የጨረታው ውጤት የሚሰረዝ ሆኖ ከላይ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል።

ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

 

ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ

ሳር ቤት ወይም አፍሪካ ህብረት ጀርባ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ

 

) 911-99-31-15/0114626090 ሪከቨሪ

☎ 011-4-70-59-08/011-1-26-31-03

 

Save Tender