Tender Detail

Tender Details

  • Company AA Kaliti Customs Office (አ.አ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት)
  • Address ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ ያለበት አዲሱ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 4403766
  • Website
  • Deadline02 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-02 00:00:00
  • Categories Office And Home Furniture , Used Items

የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ልዩ ልዩ ያገለገሉ የቤትና የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

AA Kaliti Customs Office (አ.አ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት)


 

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

  1. የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ልዩ ልዩ ያገለገሉ የቤትና የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
  2. በጨረታው ለመወዳደር የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡
  3. በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ሳሪስ አቦ ኖከ የነዳጅ ማደያ አጠገብ ከሚገኘው የናይል ኢንሹራንስ ህንፃ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 በመቅረብ የዕቃዎችን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሰነድ 100 (አንድ መቶ) ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000008635033 በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም ገቢ በማድረግ መግዛት እና ዕቃዎችን መመልከት ይቻላል፡፡
  4. ጨረታ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደሪያ ከሰጡት ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በማሰራት ዋጋ ከሰጡት ሰነድ ጋር በማያያዝ በኤንቨሎፕ/ፖስታ በማሸግ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
  5. ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ አሸናፊ ከሆኑ ተደምሮ የሚከፈል ሲሆን፣ በጨረታው ከተሸነፉ ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
  6. በተለያየ መንገድ ፍትሐዊ ውድድር እንዳይኖር በነጠላ ወይም በቡድን በሚመሳጠሩት ላይ ቅ/ጽ/ቤቱ ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል፡፡
  7. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው በ5 (አምስት) የሥራ ቀናት ውስጥ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻለ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ተደርጐ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
  8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ዕቃዎችን በ10 የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
  9. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡15 ሰዓት በቅ/ጽ/ቤቱ ቢሮ ናይል ህንጻ ጀርባ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ 011-4403766 ደውለው መጠይቅ ይቻላል፡፡

 

የአ.አ ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender