በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ንብረትነታቸው የቅ/ጽ/ቤቱ የሆኑ ያገለገሉ ሁለት ጀነሬተሮች በሎት አንድ (1) እና ያገለገሉ የተሸከርካሪ መለዋወጫዎችና የተለያዩ ብረታ ብረቶች በሎት ሁለት (2) ባሉበት ሁኔታና ቦታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
ያገለገሉ ጀነሬተሮች እና ያገለገሉ
የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ሽያጭ የጨረታ
ማስታወቂያ ቁጥር ECC-JBO/01/2017
በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ንብረትነታቸው የቅ/ጽ/ቤቱ የሆኑ ያገለገሉ ሁለት ጀነሬተሮች በሎት አንድ (1) እና ያገለገሉ የተሸከርካሪ መለዋወጫዎችና የተለያዩ ብረታ ብረቶች በሎት ሁለት (2) ባሉበት ሁኔታና ቦታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በመምጣት የንብረቶችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፣
- ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ እና ቅዳሜ 3፡00 እስከ 5፡30 ሰዓት በጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ተገኝተው እቃዎቹን መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በሚገዙት ዕቃዎች የጨረታ የመሸጫ መነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቨሎፕ በመድረግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋ እና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ሲ.ፒ.ኦ እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን መስፈርቶች አሟልቶ መገኘት ነው፡፡
- በዕቃዎች የጨረታ የመሸጫ የመነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) ያላስያዘና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች መስፈርቶችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡
- የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ወይም ሲ.ፒ.ኦ. ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ የተዘጋጀ መሆን ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ፍላጎት ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ ሙሉ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙ የጨረታ ማስከበሪያ ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡
- ቅ/ጽ/ቤቱ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በሥሙ ወይም በህጋዊ ተወካዩ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ ያለባቸው ሲሆን ይህ መሆን ካልቻለ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፣ ዕቃም በድጋሜ ለጨረታ ይቀርባል፡፡
- ቅ/ት/ቤቱ ጨረታውን መቀበል ወይም አለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻችን፡- ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 05
ተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0913220473 ወይም 0928142748
በጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
