ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ለሰራተኞች ሰርቪስ የሚያገለግል መለስተኛ አውቶቡስ ከ 30-35 መቀመጫ ያለው አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Chemical Industry Corporation (ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኬኢኮአመኬፋ 009/2017
ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ለሰራተኞች ሰርቪስ የሚያገለግል መለስተኛ አውቶቡስ ከ 30-35 መቀመጫ ያለው አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በመመልከትና በማሟላት መጫረት ይችላሉ፡- (መለስተኛ አውቶቡስ)
የሰራተኛ መለስተኛ ሰርቪስ መኪና አይነት ኮስትር ባለ 30-35 መቀመጫ ያለው ብዛት 1 (አንድ) ስለሆነም፡-
- ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ጨረታውን መሣተፍ ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከአዲስ አበባ ሳሪስ አቦ መርቲ ህንጻ የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ዘወትር በስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ መግዛት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ወይም በባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ቼክ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች ለሚያቀርቡት መኪና ዝርዝር ስፔስፌኬሽን ማቅረብ አለባቸው፡፡ ቴከኒካል እና ፋይናንሺያል ኦፈር ለየብቻ ኦርጅናልና ኮፒ በሰም በታሸገ ፖስታ እስከ ሀምሌ 2 ቀን 2017 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ ሰነዶቹን በአዋሽ መልካሳ ዋና መስሪያ ቤት ከአዳማ 15 ኪ.ሜ ወደ አሰላ በሚወስደው አስፋልት ዳር ባለው ፋብሪካው ግቢ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ሀምሌ 2 ቀን 2017 ዓ.ም በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ዋናው መስሪያ ቤት በድርጅቱ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ፋይናንሺያል ኦፈር መክፈቻ በቴክኒካል ኦፈር መክፈቻ እለት ይገለጻል።
- ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- ስልክ 09 20 93 53 36/ 022 22 502 66/
አመኬፋ
