ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Berhanena selam printing enterprise (ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት)
የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በጨረታ አንድ (ሎት 1) - Bound Bright Stiching wire No 20 ብዛት 600 ጥቅል ፤ Ivory Board 61x86cm 250 GM ብዛት 130,000 ቅጠል፤ White Art paper 61x86cm 80gm ብዛት 50,000 ቅጠል፤ White Art paper 61x86cm 300gm ብዛት 50,000 ቅጠል፤ Blue Manilla paper 61x86cm 250gm 100,000 ቅጠል እና Blue Tella ብዛት 7,000 ሜትር ግዥ፤
በጨረታ ሁለት (ሎት 2) - የፕሪንተር ቀለም (ቶነር) Kyocera TASKalfa 4004i/5004i/6004i/7004 i ብዛት 60 ግዥ፣ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ።
ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ አዲስ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 300.00 ከፍለው በመግዛት ፋይናንሻል የቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባሩ ህንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሎት 1 ለተዘረዘሩት ብር 20,000.00 እና በሎት 2 ለተጠቀሰው ብር 10,000 በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው:: ጨረታው በ8/11 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰአት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች፣ የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ህንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡ የፋይናንሻል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት ቴክኒካል ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው፡፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡
ስልክ ቁጥር 011-1-55-52-30
ድረ-ገጽ (www.ethbspe.org)
Berhanena Selam Printing Enterprise
አዲስ አበባ
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት
