በሀዲያ ዞን ጎምቦራ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች (መኪናዎች እና ሞተር ሳይክሎች) ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በሀዲያ ዞን ጎምቦራ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በሀዲያ ዞን ጎምቦራ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች (መኪናዎች እና ሞተር ሳይክሎች) ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡-
ሎት - 1 መኪናዎች
ሎት - 2 ሞተር ሳይክሎች
- ተሽከርካሪዎቹ የሚገኙበት አድራሻ በሀዲያ ዞን ጎምቦራ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት እና በሀዲያ ዞን ፖሊስ መምሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛሉ።
- በተሽከርካሪዎች ጨረታ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሆነ ግለሰብ ወይም ድርጅት መሳተፍ ይችላል።
- ተጫራቾች ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድና የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም እና የተጫራቾች መመሪያ ጋዜጣው አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ በተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ በእያንዳንዱ ተሽከርካሪ በተናጠል፡- ሎት 1 መኪና ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ እና ሎት -2 ሞተር ሳይክል ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ የማይመለስ ብር በመክፈል በሀዲያ ዞን ጎምቦራ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 01 በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩትን ተሽከርካሪ/ዎች በሎት በተናጠል ወይም በድምር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የመነሻ ዋጋ 20% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
- የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋ መሙያ መምሪያው ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት የመወዳደሪያ ፖስታ አንድ ዋና /Original/ እና ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻ በፖስታ ታሽጎና እንደገና ሁለቱም በአንድ ፖስታ ውስጥ ተካቶ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 01 ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ዋጋውን በግልጽ በአሃዝና በፊደል በመጻፃፍ በእያንዳንዱ በቀረበው ዋጋ ፊት ለፊት በፊርማ ማረጋገጥ አለባቸው ያልተፈረመ ሰነድ ዋጋ አይኖረውም።
- ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መሠረት ከአንድ በላይ ተሽከርካሪ መጫረት ይችላሉ።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው/አስራ ስድስተኛው/ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ8፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የበዓል ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።
- ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሽከርካሪዎች አሸናፊነታቸው በደብዳቤ በተገለጸ በ10 /አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ ማንሳት አለባቸው ሆኖም በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ገዢው ካላነሳ ለሚደርሰው ለማንኛውም ችግር ሻጭ ተጠያቂ አይሆንም።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ከመንግስት የሚፈለግ ግብርና ቀረጥ በሻጩ የሚሸፈን ይሆናል።
- አሸናፊው ተጫራች የተሸከርካሪ ስም ማዘዋወሪያ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ወጪዎች በሙሉ በአሸናፊው ይሸፈናል።
- ተጫራቾች የመነሻ ዋጋ እና የዋጋ ማቅረቢያ የጨረታ ሰነድ አካል ሲሆን ከጨረታ ሰነድ ጋር የተያያዘ ነው።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- በስልከ ቁጥር 0916187048/ 0923447936/ 0934129404/ ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በሀዲያ ዞን ጎምቦራ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
